አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
በባህር ደር በሁለት ወጣቶች ላይ በደረሰ ጥቃት አንደኛው ወዲያው ነፍሱ ሲያልፍ ሌላኛው ክፉኛ ተጎድቶ በህክምና ላይ እንደሚገኝ ታወቀ።
በአሰቃቂ መንገድ የተገደለው ወጣት በአከባቢው በባጃጅ ሹፌርነት የሚተዳደር እንደነበረም ታውቃል። የሞተውም በደረቱ ላይ በተተኮሰበት ጥይት መሆኑንም የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በጥቃቱ የቆሰለው ወጣት በክልሉ በሚገኝ የጤና ጣቢያ በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ እንደነበረም መረዳት ተችሏል።
በቁጥር ወደ አምስት የሚደርሱ የአገዛዙ ታጣቂዎች በእነዚህ ሁለት ወጣቶች ላይ ተኩስ እንደከፈቱባቸውና እንደተሰወሩ እማኞች ገልጸዋል።
አምስቱ የወያኔ ታጣቂዎች ታካሚዎች በመምሰል ወደ ጤና ጣቢያው በመዝለቅ ባደረሱት ጥቃት አንደኛው ወጣት ወዲያውኑ መሞቱንና ሌላኝው እግሩ መመታቱና መቁሰሉን እማኞቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በባህር ዳር በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የሚደርሰው ግድያና ጥቃት እየተስፋፋ መጥቷል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የአገዛዙ ታጣቂዎች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የብቀላ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኙ ይናገራሉ። መንግስት ይህንን ውንጀላ የሚያስተባብልም ሆነ የሚደግፍ ምንም አይነት ምላሽ እስካሁን አልሰጠም።
በባህር ዳር ግራንድ ሆቴል የደረሰውን የቦምብ ጥቃት መሰረት በማድረግ የውጭ አገራት ጎብኝዎች ወደ ክልሉ እንዳይጓዙ ማስጥንቀቂያ መሰጠቱ ይታወሳል።
እነዚህ ግድያዎችና የቦምብ ጥቃቱ የገዢው መንግስት በአማር ክልል በአስቸኩዋይ የጊዜ አዋጁ ያሰበውን ህዝቡን በአጭር ጌዜ የማፈንና የማንበርከርክ እቅድ እንዳልተሳካለት ማሳያ ሊሆኑ ይችላሉ።
No comments:
Post a Comment