Saturday, January 21, 2017

ለወገን ይድረስ!…… ከወያኔ ደህንነት አፈትልኮ የወጣ

ከወያኔ ደህንነት አፈትልኮ የወጣ*አዲስ የጥቃት ስልቶች!
መልእክቱ ከትንሽ ማስተካከል ውጭ እንዳለ የቀረበ ነው።
ወያኔ ያልሞከረችው የለም። አሁንም ትልቁ የራስ ምታት የሆኑባቸው ወደ ታች ቆላ ወገራና አዲስ ዘመን አሉ ተብለው ከመንግስት ባልተናነሰ ሁኔታ አቅም ያላቸው ታጋዮች የሚባሉት ያልጠበቁትን ያህል ትጥቅ እና ተከታይ ስለያዙ እንዲሁም በፍጥነት ቦታ መቀየር እና እንዲሁም ተወርውረው INFO..የሚያደርሱ ተቆርቋሪ ስላሉ ተቸግረዋል፡፡
ስለዚህ የሰሜን እዝ ብቻ ሳይሆን ታማኞችም ተቀላቅለው ያችን አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ መስራት ይፈልጋሉ፡፡ በመጀመርያ ለሽፍታ ከአካባቢው ከራቁ ችግር የለም ብለው ነበር። ነገር ግን በታች መረብ ወንዝ ድንበር አሁን ወያኔ እያጠበበው ቢመጣም ቅሉ ትጥቅ ማስገቢያ…ተብሎ ስለታሰበ ቅድሚያ እነሱን ለመደምሰስ ወያኔ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞራል የሌለው ወታደር አስፍሯል፡፡
ይህ አይደለም የሚያስፈራው። ምክንያቱም ታጋዮች ምን ሰርተው እንደ ሚያልፉ ስለሚታወቅ ነው። ግን የሠፈረው ወታደር የሚደርስበት ኪሳራ ማንም የማይገምተው አይነት ስለሆነበት በተለያዮ የማይመሥሉ ዘዴዎች ዘምተዋል። የተባሉ ቤተሰቦችን እንዲሁም ጥላቻ አላቸው የሚባሉትን ወገኖች በመለየት ሲቭል ለብሠው ያሉበትን በማጥናት ላይ ናቸው፡፡
በመቀጠል የአማራን መሣርያ የመንጠቅ ፕሮግራም ከውስኖቹ ያውም ኃላፊነት ካላቸው ውጭ እንዳያውቁት ብቻ ሳይሆን እንዳይገምቱም አድርገው ነዉ ሌት ተቀን የሚሰሩት፡፡ስለዚህ የአማራ አርሶ አደር ሳምንታዊ ገበያ ቀን አይደለም ትላልቆቹ ትንሾቹ ሳይቀሩ ለገበያ ሸክም መረዳዳት ሲባል ሁሉም ይወጣል በዚህ ቀንም ቅስም ሰባሪ የመንጠቅ ስራ ይሰራል። ከገበያም በላይ እሁድ እሁድ ቤተ-ክርስቲያን ከ 1-4 ሰዓት ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ከቤታቸው የሉምና፡NETWRK በማጥፍት ሊሞክሩ ይችላሉ። ደግሞም እኮ ከ3 ወር በፊት ተሞክሮ የተወሰነ ጦር መሣርያዎች ወስደዋል፡፡ሌላው አንድ ለወያኔ ቅርብ የሆነ መረጃ የሚያገኝ ሰው ያለኝ በከፍተኛ ሁኔታ አክቲቪስት ተመድቦ አማራና ቅማንትን ለማጋጨት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ደም ማፋሰስ እና ለሁልጊዜ ቅራኔ መፍጠር እንዲቻል እየሰሩ ነው።


ሙሉነህ ዮሃን

No comments:

Post a Comment