Friday, January 13, 2017

ያኔ....



የቋራው አንበሳ፣ የጦቢያ ዘበኛ፣
“እጅ አልሰጥም!” ብሎ፣ ላ’ገሬ ደመኛ፣
ሽጉጥ ተንተርሶ፣ መቅደላ ላይ ተኛ።
ከመቅደላ አናት ላይ፣ የታየችው እሳት፣
ወደ ሌላው ምድር፣ አጥታ ‘ሚለኩሳት፣
ኢትዮጵያ ታመመች፣ በእንግሊዝ ትኩሳት።
ዛሬ‹፦
የአንድነቷ ድልድይ ፣ የቤታችን ማገር፣
ዳግም ስትወረር ፣ የመይሳው ሀገር...
“የወገኖቼ ደም፣ደሜ ነው” እያሉ፣
የገብርዬ ልጆች ፣በእምነት ሲጋደሉ....
ጎንደር ስትታጠር፣በሰናክሬም ጭፍራ፣
ተዋበች “ልጆቼን!” ብላ ስትጣራ፣
ከሰሜን ከደቡብ፣ ከምእራብ ከምሥራቅ፣
ያለኸው ወገኗ፣ ዋጥ አድርገህ ምራቅ፣
“አለሁልሽ” በላት፣ ሳታይ ወደ ኋላ፣
ብልጭታዋ ብርሃን፣ ምድሩን እንድትሞላ።(ደረጀ ሀ›)Image may contain: one or more people

No comments:

Post a Comment