Monday, January 16, 2017

በተለምዶ ቆራሊዮ እየተባሉ የሚጠሩት የሀገሪቱ ለውጥ በእንጀራ ገመዳቸው ላይ ስጋት መደቀኑን ተናገሩ


በተለምዶ ቆራሊዮ እየተባሉ የሚጠሩት ያገለገሉና አሮጌ ቁሶችን ወደጠቃሚነት የመቀየር ስራ የሚሰሩ ሰራተኞች የሀገሪቱ ለውጥ በእንጀራ ገመዳቸውImage may contain: 1 person ላይ ስጋት መደቀኑን ተናገሩ፡፡Image may contain: one or more people, people walking, crowd and outdoor
በኢትዮጵያ ያገለገሉ ቁሶችን ወደጠቃሚነት የሚቀይሩ ሰራተኞች የሀገሪቱ ለውጥ ስራቸው ላይ ስጋት መደቀኑን ተናገሩ

በተለምዶ ቆራሊዮ እየተባሉ የሚጠሩት ያገለገሉና አሮጌ ቁሶችን ወደጠቃሚነት የመቀየር ስራ የሚሰሩ ሰራተኞች የሀገሪቱ ለውጥ በእንጀራ ገመዳቸው ላይ ስጋት መደቀኑን ተናገሩ፡፡

ይህ ኢ-መደበኛ የሚባል ዘርፍ በየመንደሩ እየማሰኑ ያገለገሉ ቁሶችን ሰብሳቢ ከሆኑት ከቆራሊዮዎች በተጨማሪ እቃውን ተረክበው ወደ አዲስ አገልግሎት የሚቀይሩ በርካታ ዜጎችን የእለት እንጀራ እንደሚሸፍን ይነገራል፡፡

አሁን ላይ ሀገሪቱ ከለውጥና ጊዜ አመጣሽ ዘመናዊ አኗኗር ጋር አብራ እየተጓዘች መሆኑን ሚናገሩት እነዚህ ዜጎች ለውጡ አንድ ቀን ስራቸውን እንዳይቀማና ተፈላጊነታቸው እንዳያከትም በመስጋት ላይ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

በፈረንጆቹ 2013 በተደረገ ጥናት በአዲስ አበባ ብቻ 5 ሺህ ቆራሊዮዎች ሲኖሩ ቁጥራቸው 300 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ደግሞ በዚሁ ኢ-መደበኛ ስራ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የእለት ጉርሳቸውን እንደሚያገኙ ሮይተርስ ይፋ አድርጓል፡፡

ቆራሊዮዎች ቀኑን ሙሉ በየመንደሩ እየዞሩ ጥቅም ላይ የዋሉና የማይፈለጉ ቁሳቁሶችን በመግዛት ይሰበስባሉ፡፡ ይህን ቁሳቁስ በመረከብ ጠግነው መልሰው ለአገልግሎት የማዋል ስራ የሚሰሩ በርካታ ነጋዴዎች ደግሞ በተለምዶ ምናለሽ ተራ በሚባለው በመርካቶ ገበያ እምብርት ይገኛሉ፡፡

አሮጌው ቁሳቁስ ተጠግኖና ወደጠቃሚ እቃነት ተቀይሮ በመላው ሀገሪቱ ለመልሶ አገልግሎት ይሸጣል፡፡ ይህ ዝቅተኛ ቦታ የሚሰጠው ቢዝነስ እንዲህ ተመጋጋቢ ሆኖ ለረጅም አመታት መዝለቁን ነው ዘገባው ሚናገረው፡፡

አዲስ አበባ ብሎም ኢትዮጵያ በዚህ እቃን መልሶ ለጥቅም በማዋል ቢዝነስ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ጥቅሞችን ሲያገኙ ቆይተዋል፡፡ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ቢናቁም የሚያስገኙት ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ጠቀሜታ ብዙ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት በሀገሪቱ እየመጣ ያለው ለውጥና ዘመናዊ አኗኗር ይህን ቢዝነስ ከጨዋታ ውጪ ሊያደርገው ተቃርቧል የሚለው ዘገባው በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎች በዚህ ሳቢያ ያጠላባቸውን ስጋት በሰፊው ለማስቃኘት ይሞክራል፡፡

No comments:

Post a Comment