Wednesday, January 11, 2017

የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ግዕዝ ማስተማር ጀመረ ጥር 3፡2009



የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ በትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምፃዊ ዘዊኬንድ የገንዘብ እርዳታ ጥንታዊውን ኢትዮጵያዊ የግዕዝ ቋንቋ ለ25 ተማሪዎች መስጠት ጀምሯል፡፡
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጥንታዊ መፅሀፍት የተፃፉበትን የግዕዝ ቋንቋ በማስተማሩ ዩኒቨርሲቲው የግዕዝ ቋንቋ ከሚሰጥባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ አድርጎታል፡፡
ለዘመናት በቂ ጥናት ሳይደረግበት የቆየውን፣ በርካታ ታሪክና እውቀት ያዘሉ ፅሁፎች የተፃፉበትን የግዕዝ ቋንቋ በማስተማር በማሀል የተዘለለውን ታሪክና እውቀት ለማጥናት ያስችላል ተብሏል፡፡
በዩኒቨርስቲው የሩቅና የመካከለኛው ምስራቅ ስልጣኔዎች ዲፓርትመንት መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ራበርት ሆልምስቴድት በቶሮንቶ ለሚገኙ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብና አካባቢ ነዋሪዎች ለተውጣጡ 25 ተማሪች የመጀመሪያውን የግዕዝ ትምርት መስጠት ጀምረዋል፡፡
ምንጭ፡- የቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !Image may contain: one or more people, beard and textImage may contain: 1 person, sitting

No comments:

Post a Comment