Thursday, January 19, 2017

በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆና በመተማ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎች ደረሱ ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :

Bilderesultat for ኢሳት የዛሬ ዜናትናንት እና ዛሬ በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ በተባለው ቦታ ሁለት የእጅ ቦንቦች የፈነዱ ሲሆን፣ ነጋዴ ባህር በተባለ ቦታ ላይም ተመሳሳይ ቦንብ ፈንድቷል። ይህን ተከትሎም አካባቢው በወታደሮች የተከበበ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችም ታፍሰዋል። ከትናንት ጀምሮ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ጥቃቱ በነጻነት ሃይሎች መፈጸሙን ከመግለጽ ውጭ በዝርዝር ጥቃቱን ስለፈጸሙት ሃይሎች አልተናገሩም። አንደኛው ቦንብ በህወሃት የጥድ ማዳመጫ ላይ የተወረወረ ሲሆን፣ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ መቃጠሉም ምንጮች ገልጸዋል።
ጃኑላና ጫኮ ሚካኤል በተባለ ቦታ ላይም እንዲሁ የእጅ ቦንብ መፈንዳቱን ተከትሎ የጥምቀት በአል በአካባቢው ህዝብ ሳይሆን በወታደሮች ብቻ ታጅቦ መከበሩን፣ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ፍንዳታውን አካባቢውን የተቆጣጠረው የኮማንድ ፖስት ሆን ብሎ እንዳደረሰው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በገዢው ፓርቲ በኩል ግን እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም። በአሁኑ ሰአት ህዝቡን ቅማንት አማራ በማለት ለመለያየት ሙከራ እያደረገ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎችም ተይዘው ታስረዋል።
እነዚህ አካባቢዎች አገዛዙ ቀይ መስመር ብሎ የሰየማቸው ቦታዎች ሲሆኑ በተደጋጋሚ በነጻነት ሃይሎች እየተደፈሩ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

No comments:

Post a Comment