Wednesday, January 11, 2017

የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ ያሉት አስራ ሁለቱ የኤፍ ቁልፎችና አገልግሎታቸው



F1 ይህን አቋራጭ መንገድ መጠቀሚያ ቁልፍ እርዳታ ሲፈልጉ መጠቀም ይችላሉ።No automatic alt text available.
F1 ቢጫኑ “help” የሚለው አማራጭ ይመጣል ጎግል ክሮም ከሆኑም ክሮም ሄልፕ ሴንተርን ያገኛሉ፤ ከዚያም የፈለጉትን በመጻፍ መጠየቅ ይችላሉ።
F2 ይህ ቁልፍ ደግሞ ተጽፎ አልያም ከኢንተርኔት በማውረድ ኮምፒተርዎ ላይ ያስቀመጡትን መረጃ ወይም ፋይል ስም ለመቀየርና ለማስተካከል ወይም ‘edit’ ለማድረግ የሚጠቀሙበት ነው።
ምናልባት የጻፉትን ነገር ስሙን ማስተካከልና መቀየር ከፈለጉ ያንን ፋይል በመምረጥ F2ን በመጫን ማስተካከል ይችላሉ።
ማይክሮሶፍት ኦፊስ እየተጠቀሙ ከሆነ ደግሞ፥ Alt + Ctrl + F2 በመጫን የፋይል ማህደሩንም መክፈት ያስችልዎታል።
F3 ደግሞ ዊንዶው ኤክስፕሎረር ወይም ኢንተርኔት ላይ ፋይልና መረጃዎችን ለመፈለግ ይጠቅማል።
አድሬስ ባሩ ላይ በመጻፍ አንድን መረጃ መፈለጊያ ‘search’ ማድረጊያ ነው።
ማይክሮሶፍት ወርድ እየተጠቀሙ ከሆነ ደግሞ፥ Shift + F3ን በመጠቀም እንግሊዝኛ እየተጠቀሙ ከሆነ የመረጡትን ጽሁፍ በካፒታል ማስቀመጥ ያስችልዎታል።
F4 ከተጠቀሙ ደግሞ ከፍተውት የነበረውን ወርድ መዝጋት ይችላሉ፤ ለዚህም Alt + F4ን መጫን ነው።
ይህ ቁልፍ በፍጥነት ለመዝጋት ስለሚያግዝ ከፍተውት የነበረውንና ሌሎች እንዲያዩት የማይፈልጉትን የወርድ ፋይል በቶሎ ለመዝጋት ያስችልዎታል።
F5 ኮምፒውተር በተለይም ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ይህን ቁልፍ በሚገባ ያውቁታል።
ይህን ቁልፍ በመጫን ኮምፒውተሩን ‘refresh’ ለማድረግ ያግዛል።
ከዚህ ባለፈም ኢንተርኔት እየተጠቀሙ Ctrl+F5ን ከተጫኑ የከፈቱትን አንድ ታብ ብቻ ‘refresh’ ለማድረግ ያግዛል።
F6 በመጠቀም ማይክሮሶፍት ኦፊስ ላይ ከዴስክቶፑ ወደ ሌሎች ፋይሎች ይወስዳል።
ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ላይ ደግሞ F6ን በመጫን ወደ አድሬስ ባሩ መድረስ ይቻላል።
F7 ብዙ አገልግሎት የለውም
F8 ምናልባት ኮምፒውተሩን እያበሩ ከሆነ ስራ እስከሚጀምር የሚወስደውን ጊዜ ለመቀነስ F8 ሲጫኑ በኮምፒውተሩ Start Menu እንዲገቡ ያስችልዎታል።
F9 ይህ ቁልፍ ደግሞ የኮምፒውተር ፕሮግራመር ለሆኑት የሚጠቅም ነው።
እነዚህ ባለሙያዎች Ctrl+F9 በመጠቀም ፕሮግራሙን በአንድ መሰብሰብና የሚጠቀሙበትን ኮድ ማስጀመር ይችላሉ።
F10 ማይክሮሶፍት ኦፊስ የሚጠቀሙ ከሆነ F10 በመጫን የወርዱ መግቢያ ወይም Menu bar ላይ የፈለጉትን ለመምረጥና ለመገልገል ያስችልዎታል።
ከዚህ ባለፈም Shift + F10ን በመጫን ፋይሉን ኮፒ ለማድረግ እና ለመገልበጥ፣ ለማስተካከል፣ ለማጥፋት የሚጠቀሙበትን ወይም ሌሎች አማራጮችን ለማግኘት ያስችልዎታል።
ይህም ማውዙን በቀኝ በኩል ክሊክ ሲያደርጉት የሚመጡትን አማራጭ Shift + F10ን በመጠቀም ማግኘት ይቻላል።
Ctrl + F10ን በመጫን ደግሞ የሚሰሩበትን ወርድ ማሳነስና (minimize) በማድረግ፥ በኮምፒውተሩ ስክሪን ሌሎች ስራዎችን የመስራት አማራጭ ያስገኝልዎታል።
F11 ቁልፍ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ ከተጫኑት የኮምፒውተሩን ሙሉ ስክሪን እንዲያዩ ያስችልዎታል።
F12 ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ሆነው F12 ሲጫኑ እየጻፉት ያለውን ፋይል ማስቀመጫ መንገድ Save As አማራጭ ይመጣልዎታል።
እርስዎም ከፈለጉ ባለበት አልያም በሌላ አማራጭ ተጠቅመው ማስቀመጥ ይችላሉ።
ምናልባት የጻፉትን ዶክመነት ፕሪንት ማድረግ ከፈለጉ ደግሞ Ctrl + Shift + F12ን መጠቀም ይችላሉ።
ያን ጊዜም የመጣውን አማራጭ ተጠቅመው ፕሪንት ለማድረግ ማዘዝ ያስችልዎታል።
ይህን ፕሪንት የማድረግ አማራጭ በማይክሮሶፍት ኦፊስ ላይ ሲሆኑ፥ Ctrl + P በመጫን ማግኘትም ይችላሉ።

No comments:

Post a Comment