የአስቸኳይ ጊዜው አዋጁ እንደሚራዘም ተመክሮበታል!
ወያኔ ከ3 ሳምንት በፊት ከሀገሪቱ በሙሉ ከሚገኙት ዞኖች/ክፍለ ከተሞች በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ብቻ ሳይሆን በህወሃት ስለት የተገረዘ አእምሮ አላቸው ብሎ የሚመካባቸውን በየዞኑ ከ2-5 ካድሬወች በተለይም አማራና ኦሮሚያ ክልል(የህዝብ አመፅ ከሚበዛባቸው) አካባቢ በርካታ ታማኞችን በ4 ማዕከል(አ.አ፣ መቀሌ፣ ባህርዳርና አዳማ) እስከ 24/05/09 ዓ.ም የሚቆይ ብርቱ ስብሰባ ነው።
መኃላቸውን ከአማራና ከቤንሻንጉል ጉምዝ የመጡት ታማኞች አንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ በሚከተለው መልኩ ቆይታቸውን አውስተው በሞቅታ መጫወቻ እንዳረጓቸው የተሻለ የህዝብ ስሜትና ወገንተኝነት የተሰማቸው በብስጭት ከወገናቸው ጋ እራሳቸውን ነፃ ለማውጣት እንደሚሰራና በተለያየ ሁኔታ ስርአቱን እርቃኑን እንደሚያስቀሩት አቋም መያዛቸው ታውቋል።
ይህን ጉዳይ እንዲህ ነው ያስኬዱት፡-
1. አ.አ ሲቭል ሰርቪስ ዪኒቨርስቲ በፕላዝማ የሚመሩት ካሳ ተክለብርሃን፣ በረከት ስሞኦን እና ሌሎቹ ለታዳሚዎች የተነገረን ጠንቅቀን ማወቅ እና የሞት ሽረት ውጊያችን እስካሁን ያላሸነፈው አንዱ ትግል ቢኖር የነ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ድብቅና የውስጥ ቡርቦራ አካሄድ ነው፡፡ ለዚህም ክፍተቱን በመስጠት ያገዝነው እናንተ እና በየደረጃው የተማረውን ወጣት የስራ ቅጥር እንዲያገኝ ባለመሆኑ ነው ተብለናል፡፡
2. እንዲሁም አማራ ክልል በተለይም ሰሜን ጎንደር ዙርያ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በወልቃይት ሰበብ እነሱ እና ቤተሰቦቻቸው ትግሉን ተቀላቅለዋል። ታድያ ይህን ከስሩ ለማምከን ያሉትን ባስቸኳይ የወጡትን በጥበብ የማስመለስ ሚናው የማንም አይደለም የናንተ እንጂ ተብሏል፡፡
3. ስለእንል ጃዋር መሀመድ ቦታ ሰጠውም አወያዩ በረከት እንዳለው እጅግ ፈጣን አስቸጋሪና ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኑን እናውቃለን OMN ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለን ስናዘጋ በሌላ ይመጣል። ብዙ የኦሮሚያ ወጣቶችም ይሰሙታል። በዚህም የተነሳ ያላቸውንም ንብረትን በማውደም አሁን ለደረሰው የeconomy መጎሳቆል ጥሎናል፡፡ይህንንም ለማስቆም ሳንፈልግ የወጣቶቹን ሒወት ቀጥፈናል።
4. ቀጥሎም ካሳ ተክለ ብርሀን በግልፅ ማውራት ስላለብን ነው በኤርትራና በግብፅ በሚረዳው የግ.7 ሒደት ውስጥ ኦነግ ቢኖርም ወደ ሀገራችን ዘልቆ የመግባት አቅም የማይኖረው የሚንቀሳቀሱበት መልክአምድራዊ አቀማመጥና ያካባቢው ማህበረሰብ ልክ እንደ አማራው የጦር መሳርያ ያልታጠቀ ስለሆነ እንዲሁም በመከላከያ ኃይል ብርታት የተገታ ሆኗል፡፡ እዚህ ላይ መገንዘብ ያለባቹህ አለ ለኛ የሚደርሰን እሳት የዘገየ ነው ቅድሚያ ባሰቃቂ ሁኔታ ትኩረት ወስደው የሚያጠፏችሁ እናንተን ነውና ተግታችሁ ስሩ ብሏል።
5. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በፍጥነት ባናውጅ አሁን የለንም ነበር እጅግም መቆሚያ አጥተን ተንገዳግደን ነበር። ስለዚህ ጠቀሜታው የጎላ ስለሆነ ለቀጣይ 4 ወራት እንዲራዘም የምንጠይቅ ይሆናል። በዚያ ጊዜም የምንሰጠውን ተልእኮ ባግባቡና በታማኝነት ከሰራችሁ የህዝብ አመፁ የሚከስም ይሆናል፡፡
6. የበለጠ የትኩረት እይታችን ግን አብሮን መኖሩ ሳያንሰው መጠነ ሰፊ የውጊያ አድማሱን እያሰፋ በዲያስፖራ በኩልና በሌሎች ተቆርቋሪ መሳዬች በአማራው በተለይም የጎንደር ህብረት በመባል የሚረዳ ወጣት ብቻ ሳይሆን የመከላከያ ኃይላችንም ጭምር እንዳለ ስለተደረሰበት የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን። በሰሜኑ ዙርያ በልዮ አጀንዳ መጨረሻ አካባቢ በማስመር እንወያያለን በማለት ውድቀታችንን አምነን ከገባንበት ዝቅጠት ለመውጣት እናንተ የማይተካ ሚና ተጥሎባችኀል ተብሏል፡፡
7. ከቤ.ጉ. የመጡ ታማኞችንም ውረፋ እና ንቀት በተቀላቀለ መልኩ ከአማራው ጋር ባለው አጎራባች ቀጠና ያለው የክልሉ አሸባሪ ኃይሎች እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚከስም ለብቻ ትኩረት ሰጥተን ተልኮ የምትወስዱ ይሆናል ተብለዋል፡፡
8. ከግ.7 ጋ በተያያዘ የኢሳት ጣብያን በመዝጋት ብዙ እንደተሠራና አንዳላዋጣ አሁን እንደ ትልቅ ችግር ቀርቧል።
አጣዳፊ የጥንቃቄ እርምጃወች!
#ወደ አይማ አካባቢ ፀረ ሽምቅ ተልኳል ጥንቃቄ ይደረግ። ከጃዊ ወደ ውስጥ ከአንካሻ ገብሬል እስከ ጃቫ ለራሳቸው ታማኝ ነው ብለው ላመኑት አርሶ አደር አደራ በመስጠት የወያኔው ልዩ ሃይል ወታደር ወደ ቋራ አትኩረዋል።
#ወገራ ላይ እስከ 300 የሚጠጋ ሠራዊት ካምፕ ጥሎ ወሳኝ መረጅ እየሰበሰበ ነው። በማታ ዋርድዮች ካምፑን በርቀት አካለው ነው የሚጠብቁት ምክንያት ስጋት ስላላቸው ስለዚህ የማጥቃት ስራ የሚሰራ ሀሳብና አቅሙ ካለ ይህን ግምት ውስጥ ያስገባ።
#አምባ ጊወርጊስ፣ ወገራ፣ ገደብየ፣ ዳባትና ደባርቅ እንዲሁም እንቃሽ በተለይ ወጣቶችን ጊዜ ሰጥተው እንደሚለቅሙ ሚስጥሩ ታውቋልና ቦታ በመቀየርና ልዩ ጥንቃቄ በማድረግ ይትረፉ።
ሙሉነህ ዮሃንስ
No comments:
Post a Comment