Wednesday, January 18, 2017

እኔ ለነጻንቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት


በኖርዌይ በርገን ከተማ
March፡ 4፡ 2017
ሰዓት፡ ከ 14 ፡ሰዓት ጀምሮ
የስብሰባውን ቦታ በቅርቡ እናስታውቃለንImage may contain: 2 people, text
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቸውም ግዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔን ዘረኛ አምባገነን ቡድን አስወግዶ ፍትህ በሰፈነበት እኩልነት ያረጋገጠ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመተካት በሚደረገው ትግል የመጨረሻውን የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ።
በዚህ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖም ምንም አማራጭ በሌለው ትግል ውስጥ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 የሕዝብን ትግል በማስተባበርና በመምራት የሚቻለውን ጥረት ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን የህዝብ ወገኖች ለትግሉ ልናደርግ የምንችለውን አስተዋጽዖ መሃል ትግሉን በገንዘብ መደገፍ ነው።
ይሄንንም አስተዋጽዖ ተግባራዊ ለማድረግ በመላው ዓለም ከሚገኙ ከ30 በላይ ከተሞች ውስጥ የኖርዌይ በርገን ከተማ አንዱ ነው።
*እኔ ለነጻነቴ ! ዓለም አቀፍ የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ * ዝግጅት
የኖርዌይ አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

No comments:

Post a Comment