Friday, January 13, 2017

፡፡ ሌባና ወንጀለኛን የሥልጠና፣ የሴሚናርና የውይይት ብዛትና ዓይነት አይለውጠውም፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ከፍተኛ ኣመራሮች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡

 ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት ብቻ የሚያረካ መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!፡፡ ጉዞው ሌቦች የበላይነት የያዙበትና የሌቦች መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!
ሕወሓት መራሹ አገዛዝ ቱባ ባለስልጣናት በተላላኪያቸው ሃይለማርያም በኩል በከፍተኛ አመራሩ ላይ ማስረጃ ስላልተገኘ እርምጃ መውሰድ አይቻልም የሚል ዲስኩር ኣሰምተውናል። ዋናውን የመንግስት ሌብነትና መንግስታዊ ሽብር እየመሩ ያሉት ከፍተኛ የሕወሓት ባለስልጣናት መሆናቸው አይካድም።Image may contain: text
ከተማ ውስጥ ካሉ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ጀምሮ እስከአነስተኛ ንግድ ድረስ ሃገሪቷን የተቀራመቷት እነዚሁ የሕወሓት ሰዎች ናቸው በውጪ ምንዛሬ ዘረፋና ከቀረጥ ነጻ እቃዎችን በማስገባት ግብር ባለመክፈል ወዘት ከንግድ ሰዎችና ከውጭ ባለሃብቶች ጋር ተመሳጥረው ሃገር በመበዝበዝ ስራ ላይ የተሰማሩ በዘመድ አዝማድ ቢዝነስ ሃገሪቷን እየበዘበዙ ያሉት እነዚሁ የሕወሓት ባለስልጥናት ናቸው። በተለያየ ጊዜያት በየሚዲያዎች እንዲሁም ከመሃላቸው ኣፈንግጠው በውጡ ስዎቻችው እይትጋልጡ ከፍተኛ አመራሮችን ልመጠየቅ ማስረጃ የለም ማለት ውሓ የማይቋጥር ንግግር ነው። ንጹሃን በየእስር ቤቱ የሚማቅቁት በጥይት እየተፈጁ ያለው ከላይ ከከፍተኛ አመራሩ በወረደ ትእዛዝ ነው። በገሀድ የምናየውን ወንጀል በገሀድ መካድ ተቀባይነት የሌለውና ከተጠያቂነት አያድንም።#MinilikSalsawi

No comments:

Post a Comment