Monday, January 16, 2017

#ልዩ ዘገባ አንድ ጎንደር ውስጥ ሰርግ የሚመራው በወያኔ ኮማንድ ፖስት ሆነ! ባንዲራና የአርበኛ ልብስ ተከለከለ! ጉድ በል ጎንደር!


ጎንደር ያለ ወራሪው ወያኔ በትላንት ዕለተ ሰንበት ጋብቻውን የፈፅመውን ወጣት ለአጃቢና ለታዳሚ የጥሪ ወረቀት አሰርቶ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ያሸበረቀ ነበር። ነገር ግን ኮማንድ ፖስቱ ሰለጥሪው ወረቀት ማብራሪያ እንዲሰጥበት ተጠይቆ አንዳንድ የሰርጉ ፕሮግራሞችን በኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ እንዲሰረዝ ተደርጓል።Image may contain: one or more people and outdoor
የተሰረዘው ፕሮግራም ሙሽሪትና ሙሽራው በሰረገላ በከተማው ጉዳናዎች የሚያደርጉት ጉዞ እና አባት አርበኞች ለብቻቸው የተሰፋላቸውን እጄ ጠባብ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ያሸበረቀ ባህላዊ ተነፋነፍ እንዳይለብሱ ተደርጓል።
ጉድ በል ሃገር!!!
++++++++++++++++++++++Image may contain: text

#ልዩ ዘገባ ሁለት
በተመሳሳይ ዘገባ ጥምቀትንም ወያኔ ልምራው እያለ ነው!

ወያኔ የተለመደውን የአውሬ ባህሪውን በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት በሚገኙ አባቶች፣ ቄሶችና ዲያቆናት ላይ እየፈፀመ ይገኛል። ሰሞኑን የጥምቀት በአልን አናከብርም፣ የህዝባችን ደም ሲፈስ ማየት አንፈልግም፣ ጥምቀት ከነፃነት በሁዋላ ነው የምናከብር በማለታቸው ወያኔ እንደ መፍትሄ የዎሰደው የተለመደውን ..... ማሰርና ማስፈራራት ነው።Image may contain: text
የጥምቀትን በአል ካላከበራችሁ አንፈታችሁም፣ የአሸባሪዎች ተባባሪ ናችሁ በማለት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን እያሰቃየ ይገኛል። በመሆኑም ቀሳውስቱ በአቋማቸው በመፅናት ሕዝብ ሲጨፈጨፍ ከምናይ እኛ እንሙት እያሉ ወያኔን በመሞገት ላይ ናቸው። ታዲያ ይህ የተከበረው የጎንደር ህዝብ የተለመደ ጀግንነቱንና ለቄሶችና ለአባቶች ያለውን አክብሮት ራሱን ከሞት በመጠበቅ አጋርነቱን እንዲገልጽ አባቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከጎንደር በቅንብሩ ለሰራቹህት ወጣቶች ምስጋና ይግባቹህ!
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment