Tuesday, January 17, 2017

ጥብቅ መረጃ.. አንባግነናዊ ዘረፋ በብሄራዊ መረጃ! !



ባሳለፍነው አመት 2007 እና 2008 ዓ/ም በአጠቃላይ የመረጃ ስብስብ ዘርፍ ተገቢውን ጥናት አካሂጃለው በማለት በሚኒስቴር ደረጃ እና ለተመረጡ የህውሀት የደህንነት ባለስልጣናት ዝርዝር ሀተታ ያቀረበውን ብሄራዊ መረጃን መሰረት ባደረገ መልኩ በ 2009 ዓ/ም ኢ-አንጻራዊ የውንብድና እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል::
እንደ ብሄራዊ መረጃው ምልከታ ከሆነ በመላው ኢትዮጵያ የተከሰተውን ህዝባዊ አምጽና በአስገራሚ ሁኔታ የተበራከቱትን የነጻነት ሐይሎች በተለይም አርበኞች ግንቦት 7 አሁን ለደረሰበት ከፍተኛ ተጽኖ ፈጣሪነት ያደረሱት ዲያስፓራዋች ናቸው ይላል::
በዚህ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ለዲያስፓራ ኢትዮጵያዊያን የሚሰጡ እና የተሰጡ የኢንቨስትመንት አገልግሎቶች እንዲቋረጡ እና በባንክ የውጭ ገቢ ተቀማጭ ንዋያትና የብድር አሰጣጥ መስተጋብር ይዘት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ከማሳሰብ አልፎ በዲያስፖራዋች የተገዙ ማንኛውም ይዞታዋች እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ ህገ ደንብ እንዲያቅባቸው ያመላክታል::
አያይዞም የህወሀት መንግስት ለዲያስፓራዋች የሚሰጠው ድጋፍ በአስቸኩዋይ እንዲያቆምና ተግባራቶቹን እንዲፈተሽ የሚያስጠነቅቅ ነው::
ይህን ተንተርሶ አጣብቂኝ ፖለቲካዊ ንዝረት ላይ የወደቀው የህወሀት ወያኔ አስተዳደር ከብሄራዊ መረጃው የቀረበውን ሐገር የማጥፋት እቅድ ተግባራዊ ባደረገ መልኩ በዲያስፓራዋች ላይ ወረራ መጀመሩን መረጃ የሰጡን ምንጮች ጠቅሰው ብሄራዊ መረጃው በማንኛውም መልኩ ከውጭ ወደ ሀገር የሚገቡ ዲያስፓራዋች ላይ የማዳከም ስልት እንዲጠቀም የሀገር ውስጥ ጉዳይ ደህንነት ሚኒስቴር ባለስልጥናት ፍቃድ ሰጥተውታል::
በመሆኑም ህጋዊ የአፈና ፍቃድ የወሰደው ብሄራዊ መረጃ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፓራዋችን አፍኖ በመጥለፍ ህገ ውጥ የገንዘብ ክፍያ እንዲፍጽሙ ማስገደዱን አረጋግጠዋል:: በዚህም መሰረት:: 1. ከደቡብ ሱዳን ወደ ሐገር ቤት የገቡ ሁለት ዲያስፖራ ባለሀብቶችን በማፈን ከያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዬን ዶላር መቀበሉን.
2. ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሐገር ቤት የገቡ 6 ግለሰቦችን በማፈን 4.9 ሚሊዬን ራንድ በግዳጅ መቀበላቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ፍንጮች በሰጡት መረጃ መሰረት ለማጣራት እንደሞከርነው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደቡብ አፍሪካ ዲያስፓራ ከአዲስ አበባ ቺቺንያ ከሚባል ሰፈር በደህንነቶች ተጠልፈው አይናቸው በጥቁር ጨርቅ ተጋርዶ ወደማይታወቅ ስፍራ ከተወሰዱ ወዲህ .... ለሳምንት ያህል ታፍነው 1 ሚሊዬን ራንድ ከፍለው የተለቀቁ ሲሆን አፋኝ ቡድን በተመሳሳይ መንገድ ከተለያየ ሀግር ወደ ሀገር ቤት የገቡ ተጨማሪ 8 ዲያስፕራዋችን ማገቱን ተናግረዋል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! !
( ጉድሽ ወያኔ

No comments:

Post a Comment