Thursday, March 23, 2017

ታላቅ የድል ዜና!


ስሙን ቆየት ብለን የምንጠቅሰው አንድ ከተማ ላይ በወያኔ ሰራዊት ላይ ሁለት ሌሊት የፈጀ ጥቃት ተሰንዝሯል! ይህ በአይነቱም በመጠኑም ከበድ ያለው ምት ወያኔን ክፉኛ አሸብሯል። ጥቃቱን ያደረሱት ጀግኖች የመንግስትን ጣብያ ሁለት ሌሊት ሙሉ ሲቆሉት አድረው በድል ተመልሰዋል። ይህ የህዝባዊ ትግሉ ያለበትን እመርታ ያሳያል። ዝርዝር ጉዳዮች መዘግየታቸውን አሁንም አስፈላጊነቱን ተቀበሉን።
የነፃነትን ጥያቄ በአፈና ማስቆም እንደማይቻል ወያኔና ጀሌወቹ እየመረራቸውም እየተጋቱት ነው። በማእከላዊና በሌሎች ማሰቃያወች እያደረሱት ያሉት እጅግ አረመኔያዊ ስቃይ ከሰማይም ከምድርም ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም።
ጀግና የማይነጥፍ ሃገር አለንና ደስ ይበላቹህ! ከጎናቸው እንቁም። አምላክ ለተገፋው ህዝባችን የመጨረሻዋን ድል ያጎናፅፍልን።
Asnakew Abebe

No comments:

Post a Comment