የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ እና ሌሎች አካባቢዎች ባካሄደው ጥቃት የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ተገድለዋል ጥቃቱ የተሰነዘረው በመከላከያ በጸረ-ሽምቅ ሚሊሺያዎችና መደበኛ የፖሊስ አባላት ላይ መሆኑን ምንጮችን ገልጸዋል።
በዚሁ ተከታታት ጥቃትም አካባቢውን ጥለው የሸሹ የስርዓቱ ታጣቂዎች በርካታ ናቸው ተብሏልንቅናቄው በሰሜን ጎንደር በጀመረው በዚሁ ጥቃት 3 ወታደሮች ወዲያውኑ ሲገደሉ ሌሎች ሃኪም ቤት ከገቡ በኋላ የሞቱም እንዳሉ ምንጮች ይጠቅሳሉ።
በተለይ በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ ገደብዬ በተባለች ከተማ በተወሰደው የሽምቅ ጥቃት የአካባቢው ፖሊስ ጽ/ቤት ላይ ጉዳት ደርሷል። በከተማዋ የነበሩት የመከላከያ፣ የጸረ-ሽምቅ እና የፖሊስ ሰራዊት አባላት ለጥቃቱ የተኩስ ምላሽ በመስጠታቸው ውጊያ እንደ ነበር ተገልጿል።
መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓም የግንባሩ ታጋዮች ወደ ጋይንት ከተማ በመግባት ከምሽቱ 2 ሰአት ተኩል ላይ በብአዴን ጽ/ቤት እና ሹመት በተባለው አስተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ ቦንብ በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸውንና ማሽቱም በተኩስ ሲናወጥ ማደሩን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ከተማ አካባቢ ዳንጉላ ጭንጫዬ በተባለ ቦታ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሸማቂዎችን ለማጥቃት በተደረገ ጥቃት የአገዛዙ ታጣቂዎች ቆስለው የአካባቢው አመራር የነበረው አበበ ታከለ መገደሉ ተነግሯል።
በታጋዮቹ ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ድርጅቱ አስታውቋል።
No comments:
Post a Comment