Wednesday, March 29, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ህይል በተለያዩ ቀጠናዎች ጥቃት መሰንዘሩ ተገለጸ

በሰሜን ጎንደር ኪንፋዝ በገላ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሃይል ጥቃት ሰነዘረ። ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው የሚገኘው ግዚያዊ የወያኔ ጦር ካንፕ ላይ ሲሆን በጥቃቱ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ የተገለፀ ነገር ባይኖርም በዘመቻው የተሳተፉ ከፈተኛ መሆኑን ገልፀውልናል።
በተደጋጋሚ በተደረጉ ጥቃት በለስ የቀናው የአርበኞች ግንቦት7 ኃይል ወደ ሰሜን ጎንደር በችንፋስዝ በገና ሲናሬ ከተማ ዘልቀው በህወኃት ታጣቂዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም በርካታ እስረኞችን ማስለቀቁ እና በከተማው ባሉ በወያኔ ታጣቂዎች እና የድርጅት አቅርቦት ዲፖ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ የህወኃት ወታደሮችን መገደላቸውን ዘግበናል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙ የሚያሳየው በወያኔ ላይ የያዘውን የወታደራዊ የበላይነት ነው፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር በሚወስደው ጥቃት የወያኔ የኃይል ሚዛን አሰላለፍ ያዛባና የውግያ ሞራል የወደቀ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment