Thursday, March 30, 2017

ወያኔ ኢሕአዴግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት ማራዘሙ ታወቀ



በኢትዮጵያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የወያኔ ኢሕአዴግ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት እንደተራዘመ አስታውቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያትና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ለምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም ያስፈለገበትን ምክንያት ብሎ ያቀረበውን ሀሳብ የአገዛዙ ልሳን የሆነው ፋና በዚህ መልኩ አቅርቧል።
አቶ ሲራጅ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የሚነሱ ችግሮችን ለመጠቀም የሚፈልጉ ፀረ ሰላም ሀይሎች እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው፣ በሁከት እና ብጥብጡ ቀንደኛ መሪዎች ከነበሩት ውስጥ አብዛኛዎቹ ቢያዙም ቀሪ በመኖራቸው እና በወረቀት ፅሁፎችን በመበተን አሁንም ሰላም እና መረጋጋትን ለማደፍረስ የሚጥሩ ወገኖች አልፎ አልፎ በመታየታቸው አዋጁን ማራዘም ማስፈለጉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በአንፃራዊነት ሰላም እና መረጋጋቱ የተሻለ ደረጃ ላይ ቢገኝም የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተጨማሪ ጊዜ ማስፈለጉን ለአዋጁ መራዘም በምክንያትነት አስቀምጠዋል። ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም በሙሉ ድምፅ ወስኗል።
ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማራዘሙ ዋናው ምክንያት ብሎ ያቀረበው ከአቅሜ በላይ እየሆነ የመጣውን የህዝብ ቁጣና ተቃውሞ ለማብረድ ነው ቢልም ከየአቅጣጫው ከነጻነት ሃይሎች የሚሰነዘርበትን ጥቃት ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ያመነበት ሲሆን አሁንም ልዩ ትኩረት አድርጎ የተወያየበትና ያሰጋኛል ብሎ በዋናናት ያስቀመጠው በድበሮች አካባቢ ኮማንድ ፖስቱ ሊቆጣጠረው የማይችል ሃይል ስለገጠመው ሳይወድ የግድ የአስቸካይ ግዜ አዋጁን ለማራዘም ተገዷል።

No comments:

Post a Comment