Saturday, March 4, 2017

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ድንበር ላይ የተነሳው ግጭት በቀል በበላይነት የሚቆጣጠረው የደቡብ ምስራቅ እዝ አዛዥ መሆኑ ታወቀ

ሕወሓትበቀጣይነት በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል አዲስ ግጭት ለማስነሳት ማቀዱን ታናግረዋል።

የደቡብ ምስራቅ እዝ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የበቀል እርምጃ አንዲወስድ ከሳሞራ የኑስ መታዘዙን ወታደራዊ ደህንነቶች ከእዙ ያደረሱት መረጃ ገልጿል።የመረጃ ደንበኞች የሆኑትና ካሁን ቀደም የተለያየ መረጃዎችን የሚያደርሱን ወታደራዊ ደህንነቶች እንደጠቆሙት የእዙ ወታደሮች ተመርጠው የልዩ ሃይሉን ልብስ በመልበስ በ አከባቢው የኦሮሞ ተወላጆች ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሕወሓት በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ለማዳከም በሚል በመጀመሪያ ከሲዳማ ሕዝብ ጋር በኣሁን ደግሞ ከሶማሌ ሕዝብ ጋር እያጋጨ በመሃል ተመሳስሎ በመግባት የዖሮሞን ሕዝብ እየፈጀ መሆኑን የጠቀሱት ወታደራዊ ደህንነቶች በቀጣይነት በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል አዲስ ግጭት ለማስነሳት ማቀዱን ታናግረዋል።ሕወሓት አጣብቂኝ ውስጥ ሲሆን ኦሕዴድ ውስጥ የተሰገሰጉ ሆዳሞች የኦሮሞን ሕዝብ እያስገደሉት መሆኑን ተናግረዋል።
በምስራቅ እዝ ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞና የ አማራ ተወላጆች ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ መስመር በመውሰድ ሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ ያሰፈሯቸው ሲሆን የሌሎች ክልሎችን በተለይ የቤንሻንጉል የትግራይ የሶማሊያ የደቡብ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮችን አቀናጅቶ የልዩ ሃይል ልብስ በማልበስ ሕዝብ እንዲጨፈጭፍ እያደረጉ መሆኑን ደህንነቶቹ ገልጸው ከዚህ ቀደም በኮንሶ እና በሱርማ የደቡብ ሕዝቦች ላይ የተወሰደው እርምጃ ወታደሮችን የልዩ ሃይል ልብስ በማልበስ እንደነበር ሳይጠቅሱ አላለፉም። #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment