Thursday, March 2, 2017

ሜሮን ጌትነት


እንደማንኛውም
ኢትዮጵያዊ....በእድልህ
ልታድግ "በእድሉ"ተብለህ
ትወለዳለህ።ቂጣና ቆሎህን
እያሻመድክ.....በኩርኩ ም
የሳምንት ውሎህን እስክትረሳ
እየተቆጋክ......።
.
.
ትንሽ ከፍ ስትል ቄስዬ
ትላካለህ....ሃ...ሁ ...በል ኣቦጊዳ
ቀጥል "መልእክተ ሃዋርያው
ወልደ ዘብዲዎስ ቀዳማዊ
ንዜ....." ዝለቅ እንግዲ
እየተባልክ ካለልህም እየተባልክ ካለልህም A=for
apple ን እየሸመደድክ
.....ተማረ ከተማረረ
እየተቀላቀለብህ ደረጃ ቆጥረህ
ትጨርሳለህ....
.
.
ትመረቃለህ
.
.
ለምርቃት የገዛሃት ሾዳ
እስክትተን...ስራ ፍለጋ
ትባዝናለህ
.
.
ስራ ትገባለህ
.
.
ከደመወዝህ ጋ ከወር ወር
ኣብረህ ለመቆየት......ከባድ
ፊዚክስ እንደሚበታትን ሰው.....
መከራህን ትበላለህ
.
.
ትበደራለህ
.
.
ኣብራህ ቢሮክ ውስጥ
ምትሰራውን ቸከስ ኣልያም
በባስ ስትሄድ የተዋወካትን
ዘይት ቆጣቢ የመሰለችህ ቺክ
ጋር ትጠቃለልና.....ልጆች
ትወልዳለህ...እነሱን ለማሳደግ
ኣፈር ትበላታለህ።
.
.
.
ወይንም ደሞ
.
ቂጥህን ወትፈህ ትሰራለህ.....
ትቆጥባለህ 24 ሰኣት
ትጠገራረለህ....
.
.
ወንጀል ትሰራለህ....መንግስት
ታጭበረብራለህ.....ትዘ
ርፋለህ...ግፍ ትሰራለህ
....የራስህን ጥቅም ለሟሟላት
ሰው ታስለቅሳለህ....ሆድህን
ሞልተሃል ...ፅዳ ያለ ቤት
ኣለክ....መኪናና ሸሚዝህ ማች
ነው..... ኣልፎልሃል!!
.
.
ትኖር ትኖርና...ታኗኑርና... ወደ
ማይቀርልህ ቤት
ትነካዋለህ.....ወይ መኪና ኣደጋ
ይደርስብሃል....ወይ ትናንት
ታይተህ በሳይለንት
ትነካዋለህ.....ወይ ደም ግፊትህ
ኣናትህ ላይ ወቶ ጠብ
ያደርግሃል....ኣልያ ጊዜው ደርሶ
ነው ከሞት የሚቀር የለም
በሚለው.....ፅጥ!!!
.
.
ፎቶህ በትልቁ ይታጠባል!!
.
.
ምፅ!!
ቤተሰብ ይደዋወልና
ይሰባሰባል.....
.
.
ጋቢያቸውን ለብሰው
ያለቅሱልሃል...ልጆችህ ኣባዬ
ኣባዬ...ሚስትህ ከለላዬ
...ጓደኞች ጓዴ ጓዴ
.
.
ምፅ!! ሲያሳዝኑ
.
.
ትገነዛለህ.... ኣራት ማዕዘን
ሳጥን ውስጥ ተሸፋፍነህ
ትገባለህ.....ኣንዳች እንኳ
ስልጣን የለህም በራስህ
ላይ....ከነበሩህ ነገሮች ሁላ
የሚወዱህ የነበሩት
ኣይከተሉህም።
.
.
ከምትወዳቸው ደሞ
ኣንዳቸውንም ኣጠገብህ
ማድረግ ኣትችልም።
.
.
ትቀበራለህ!!!!
የምር ምፅ!
.
.
ቀባሪዎችህ.... በቤትህ
የተዘጋጀውን ፅበል
ይቀምሳሉ....ነብስ
ይማር...ምናምን ይባልልሃል!
.
.
ማታ ላይ ድንኳን ውስጥ ካርታ
ይደራል። ቢራ
ይጨለጣል...ይሳቃል...
ይበላል....
.
.
3 ቀን ሲሞላህ ድንኳንህ
ይፈርሳል....ሰው ቀስ በቀስ
ይመናመናል።
.
.
ኑሮ ይቀጥላል!!
.
ህዝቤ ወደ ሌላ ለቅሶ ...ወደ ሌላ
ጉዳይ...አንተ
ተረስተሃል....ሚስትህን
ም...ልጆችህንም የእገሌ ልጅና
የእገሌ ሚስት ይቀርና የሟቹ
ልጆች ....ይባሉልሃል።
.
.
.
.
እና ሟቹ ሆይ ምን ልልህ
መሰለህ?
.
.
ኣንዳንዱ ሰው እንኳንስ
ሞቶ....ኖሮም ታሪክ የለውም!!
ምናልባት ታሪኩ የሚባል ስም
እንጂ!!
.
.
የእኛ ኣባቶች....ግን ለነብሳቸው
እንኳ ሳይሳሱ ከራስ ፍቅር
የሃገር ፍቅርን
ኣስበልጠው....በዱር በገደል
ተዋድቀው....ጠላትን ድል
ነስተው ከመገዛት ....ከባርነት...
ደም ከፍለው ቀና ብለን
እንድንኖር ነፃ ኣውጥተውናል
....ደም ተከፍሎልናል።
.
.
"እየገባን እንጂ ወገን"
.
.
...ሞትና እና ሞትም ይለያያል
ዘመዴ!!!
.
.
.
.
ክብር ከመቃብር በላይ ዘላለም
ለሚኖር ስማቸው.....ክብር
ለጀግኖች ኣባቶቻችን!!!

No comments:

Post a Comment