Wednesday, April 26, 2017

እነሆ ዋዛ እና ቁምነገር፤ ......ያው እንደሚታወቀው ህገራችን ኢትዮጵያ እንኳንስ ሌላው ቀርቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀሩ ምቹ ሁኔታ ቢያገኙ ስደትን የሚመርጡባት ሃገር ወደመሆን ተቀይራለች እና ይሄ የጋራ ችግር ነው… ይሄ ችግር እንዴት ተቀርፎ ሃገሪቱ መማረሪያ ሳትሆን መኖሪያ ትሆናለች የሚለውን ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን ትጋት ሊያደርግ ይገባል… በተለይም መንግስት ልል ነበር ለካስ ዋናው ችግር መንግስት ነው….! ….. ስለዚህ ሃገር ከመቀየር እና በስደት መከራ ከማየት እንደምንም አንድ ግዜ ሆ ብሎ መንግስት መቀየር ሳይሻል አይቀርም የሚለውን አማራጭ…. ብናየው መልካም ሳይሆን አይቀርም!..... .....ትንሽ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ አዲሱ ቀሚሷ... ትንሽ ስለ ኑሮ ትንሽ ስለ ክልል ባለስልጣኖቻችን በተለይም ስለ ኦሮሚያው ፕረዘዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ ትንሽ ስለ ሳውዲ ስደተኞች... እና መሰል ጉዳዮችን ይዘን ተከስተናል! @Abebe Tolla Feyisa

No comments:

Post a Comment