Tuesday, April 25, 2017

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ

የዴሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አለማቀፍ የወዛደሮች ቀን ሜይ ፩ ምክንያት በማድረግ 
፩፨ በሀገራች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ብቻ ከስራ ተፈናቅለው በእስር የሚማቅቁ ወገኖቻችን እንዲፈቱ እና አንባ ገነኑ ስርዓት በአገሪቱ እያደረሰ ያለውን የመብት ጥሰት ለአለም ለማሳወቅ 
፪፨ በኖርዌይ ለሚኖሩ መስራት እየቻሉ በስደተኛ መጠለያ ውስጥ ታፍነው የአእምሮ እስረኛ ለሆኑ ወገኖቻችን የስራ ፈቃድ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቅ
፫፨ የወዛደሩን መብት የሚያስከብረው ሀይል የስደተኝነት ጠያቂው መብት እንዲጠበቅ ይሰራ ዘንድ ለመጠየቅ ፦፦፦ 
በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው ሜይ ፩ እለት በጋራ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ድምፃችንን እንድናሰማ ለመላው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ያስተላልፋል

ሰልፉ የሚጀምረው 11:00 - 12:45 ስለሚሆን አስቀድመን እንድንገኝ እናሳስባለን ::
ቦታው Youngstorget ( Torggata, 0181 Oslo)

No comments:

Post a Comment