ታጋዮቹ በላኩት መግለጫ መጋቢት 25 ለ 26 ሌሊት ከ 7፡00 እስከ 9፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰራቫ ጣና በለስ መስኖ ፕሮጀክት ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ መሽጎ በነበርው የህውሐት መከላከያ ሰራዊት ላይ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት በወሰዱት እርምጃ ሁለት የገዥው ፓርቲ ወታደሮችን እና ሁለት የመከላከያ ሾፌሮችን ሲገድሉ በስድስት ወታደሮች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ አድርሰዋል።
የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው ወታደሮች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፤ ከመካከላቸው ክፉኛ የቆሰሉት ሁልቱ ወታደሮች ማንቂያ ክፍል መሆናቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተጠቀሰው ዕለት ሌሊት ከ5:00 እስከ 7:00 ሰአት ባለው ጊዜ በቆላ ድባ ከተማ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ስለተፈጸመው ጥቃትና ስለደረሰው ጉዳት የዝግጅት ክፍሉበማጣራት ላይ ነው።
የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ህወሃት በአምሰተ ኦራል ተሽከርካሪ የተጫኑ ወታደሮችን ወደ ቦታው እያስገባ መሆኑን የገለጹት ታጋዮቹ፤ የህብረተሰቡ ይህን አውቆ እንደተለመደው ከአርበኞች ግንቦት 7ታጋዩች ጎን በመቆም እዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።በኦራል ወደ አካባቢው እየገባ ያለው የወያኔ ወታደር የህዝቡን ትጥቅ እንዲያስፈታና ድብደባ እዲፈፅም ከአለቆቹ ትዕዛዝ እንደተሰጠው መረጃው እንደደረሳቸው የጠቀሱት ታጋዮቹ፤ ሰራዊቱ ከዚህ እኩይ ተግባርበመታቀብ አፎሙዙን ወደ አለቆቹ እዲያዞር እና ከህዝብ ጎን እንዲቆም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የመረጃው ምንጭ ኢሳት
No comments:
Post a Comment