Sunday, April 2, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በህወአት ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ቀጥለውበታል



በ22/07/2009 ዓ/ም ሌሊት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ቃኚ ሀይል ለቅኝት በሚንቀሳቀስበት ሰዓት ከሌሊቱ 6፡00 ሲሆን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማን አለፍ ብሎ ከሚገኝው ቁልቋል በር ከከተባለው ቦታ ላይ ሲደርሱ የወያኔ ባለስልጣናትን የያዘ ደብል ጋቢና ፒክአፕ መኪና ለትራንፎርሜሽን እቅዱ መሳካት የተሰጠ የሚል ከጎኑ የተፃፈበት ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል።
 ባለስልጣኑ ቆስሎ ባህርዳር ሆስፒታል ለህክምና የገባ ሲሆን አጃቢው ሳጅን አለኸኝ የተባለው ተገድሏል የሟች አስከሬን ወደ አዲስ ዘመን ፎገራ ቀበሌ ለቀብር የተወሰደ ሲሆን ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ካወጀበት ጊዜ አንስቶ የጤና ፤ የትምህርት ፤ ግብርና እና ሌሎች የሚንስትር መስሪያቤት በእርዳታ ያገኛቸውን ተሸከርካሪዎች ለፀጥታ ስራ በሚል ህብረተሰቡን ላማፈን ወታደሮች ለማመላለስ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ መስታውቱን ጥቁር በመለጠፍ ከውጭ ወደ ውስጥ ለማየት ፍፁም በሚከለክል ሁኔታ ለአፈናው በዋናነት እየተጠቀመባቸው ይገኛል ፡፡

No comments:

Post a Comment