Wednesday, April 26, 2017

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ሜይ ዴይ - አለም አቀፍ የወዛደሮች ቀን May - 1 - 2017

#Ethiopia Happy #May Day 2017
የዴሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ዓለም አቀፍ የወዛደሮች ቀን MAY 1ን ምክንያት በማድረግ
1.- በሐገራችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ከስራ ተፈናቅለው በእስር የሚማቅቁ ወገኖቻችን እንዲፈቱ እና አንባ ገነኑ ስርዓት በአገሪቱ እያደረሰ ያለውን የመብት ጥሰት ለአለም ለማሳወቅ !!!
2- በኖርዌይ ለሚኖሩ መስራት እየቻሉ በስደተኛ መጠለያ ውስጥ ታፍነው የአእምሮ እስረኛ ለሆኑ ወገኖቻችን የስራ ፈቃድ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቅ!!!
3- የወዛደሩን መብት የሚያስከብረው ሀይል የስደተኝነት ጠያቂው መብት እንዲጠበቅ ይሰራ ዘንድ ለመጠየቅ !!!
በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው ሜይ ፩ እለት በጋራ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ድምፃችንን እንድናሰማ ለመላው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ያስተላልፋል !!!!!!!!

*ሰልፉ የሚጀምረው የፊታችን ሰኞ May 1/2017 ,ከ11:00 - 12:45 ሰዓት ስለሚሆን አስቀድመን እንድንገናኝ እናሳስባለን ::
ቦታው Youngstorget ( Torggata, 0181 Oslo)

No comments:

Post a Comment