በነገው እለት በአብዮት አደባባይ የሚካሄደው ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ በየግል ወጥተን በአጋዚ ወታደሮች እና በሆድ አደር ህወሀቶች እንዳይጨናገፍ በህብረት ለመጓዝ ብሎም መድረሻችን አብዮት አደባባይ ለመድረስ እንዲያመቸን መንገዶች የተዘጋጁ ሲሆን በቀጣዩ መልክ ተያይዘን በአምስት መስመሮች ወደአብዮት አደባባይ እናመራለን።
1, የፈረንሳይ፣ የሽሮሜዳ፣ የስድስት ኪሎ፣ የቀበና፣ የአቧሬ፣ የካዛንቺስ እና የቤላ ወጣቶች አራት ኪሎ ላይ በመገናኘት በጋራ ጉዞ ወደአብዮት አደባባይ
2, የኮልፌ፣ የመርካቶ፣ የአስኮ፣ የአዲሱ ገበያ፣ የጉለሌ፣ የእንቁላል ፋብሪካ እና አጎራባች ሰፈሮች ወጣቶች ፒያሳ በመገናኘት በጋራ ጉዞ ወደአብዮት አደባባይ
3, የሲኤምሲ፣ የኮተቤ፣ የካራ፣ የገርጂ፣ የጉርድሾላ፣ የአያት፣ የሰሚት፣ የ24፣ የቦሌ፣ የሾላ፣ የ22 ወጣቶች መገናኛ ላይ በመገናኘት ጉዞ ወደአብዮት አደባባይ
4, የቃሊቲ፣ የአቃቂ፣ የቦሌ ቡልቡላ፣ የሀናማርያም፣ የጎፋ፣ የሳርቤት እና የአካባቢው ወጣቶች ሳሪስ ላይ በመገናኘት ጉዞ ወደአብዮት አደባባይ
5, የአየር ጤና፣ የጆሞ፣ የመከኒሳ፣ የቤቴል፣ የጦርሀይሎች፣ የልደታ፣ የካረቆሬ፣ የአብነት፣ የጨርቆስ፣ የቄራ እና አካባቢው ወጣቶች ሜክሲኮ ላይ በመገናኘት ጉዞ ወደአብዮት አደባባይ
ማሳሰቢያ:- ሁላችንም ወደታላቁ ህዝባዊ የተቃውሞ መድረክ ስናመራ ከቀይ ካርድ እና ወረቀት ውጭ ሌሎች ምልክት ያለባቸውን ምንም አይነት አርማዎች መያዝ የሌለብን ሲሆን ከተዘጋጁት መፈክሮች ውጭ በግል መፈክር አዘጋጅታቹህ ወደአብዮት አደባባይ የምታመሩ ሰልፈኞች መልእክቶቻችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ቢሆኑ መልካም ነው።
No comments:
Post a Comment