Friday, August 19, 2016

በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ኦገስት 19.2016 ቁጣና እልህ የተሞላበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአንድነት አካሂደዋል።እንደሚታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ በጣም በአደገኛ ችግር ውስጥ ትገኛለች። በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄአቸውን ያቀረቡ ዜጎች በአጋዚ ጥይት ህጻን አዋቂ ትንሽ ትልቅ አዛውንት ሴት ነብሰ ጡር ሳይል በአደባባይ እየተገደሉ ደማቸው እንደ ውሃ በየአውራ ጎዳናው ላይ በከንቱ እየፈሰሰ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ከሆነ ውሎ አድርዋል። ህወሃት በህዝቦች ላይ የሚፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ፣የአማራና የሌሎችም ክለሎች ወገኖቻችን በየ እስር ቤቱ ታግተው እየተሰቃዪ ይገኛሉ።ህወሃት የሚመራው መንግስት ጉዳዩን የተባበሩት ምንግስታትም ይሁን ሌሎች የሰባዊ መብት ተሟጋቾች እንዳይመለከቱት ዝግ ማድረጉ ይታወቃል ባጠቃላይ በህዋሃት ያልተሰቃየ፥ያልተፈናቀል፣ያልታሰረ፣ያልታፈነ ያልተረሸነ ያልተሰደደ ዜጋ የለም!!!! በዚህም ሳብያ በተለያዪ ክፍለ አለማት የሚገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን የወያኔን ኢሰብአዊ ድርጊት ባስቸኳይ እንዲቆም ባሉበት አገር ጩህታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ ዛሬም በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሀዝቡን ስቃይና እንግልት በሶትና መገፋት ድብደባና እስር ለኖርዌይ መንግስትና ለአለም መንግስት ለማሳወቅና በአንድ ሃይል በመተባበር በህዋሃት አፓርታይድ ስር የወደቀውን ውገኖቹን ከጎንህ ነን በማለት አጋርነቱን አሳይቷል ሰለፉ በሰንደቅ አላማ ያሸበረቀና የተለያዪ መፈክሮች የተስተጋቡበት ሲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት የተሰበከበት ነው።00543

No comments:

Post a Comment