Friday, August 19, 2016

ነጋሪቱ ተጎስሟል፣

ነጋሪቱ ተጎስሟል፣ ፋኖም ተሰማርቷል፣ ትግሉም ዘመኑ በፈቀደው ሁናቴ ደረጃ በደረጃ እያደገና እየተቀጣጠለ በመሄድ ላይ ይገኛል፤ የጊዜ ጉዳይ ነው፤ እንደኛ ጥንካሬና ድክመት በቶሎ ወይም ሰነባብቶ ነጻነታችንን እንጎናጸፋለን! ማን ነበር “የወያኔ እስከዛሬ በአምባ-ገነንነት በስልጣን ላይ መኖር የኛ ድክመት እንጂ የወያኔ ጥንካሬ አይደለም” ይል የነበረው?
ይህ በምስሉ ላይ የምታዮት ሰው (አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ) እና ሌሎች ምስላቸውን ለመለጠፍ ይህ ገጽ የማይበቃኝ ጀግኖች ወያኔን በየአቅጣጫው ጠልፈው በግር ብረት ጠፍረውታል! ወያኔ እየታበየ እንጂ አቅም ኑሮት አይደለም እየተወራጨ ያለው፣ ከኛ የሚጠበቀው - ገፍትሮ መጣል ብቻ ነው!!
ነጻነት ይቅደም እንጂ ፍቅሩንማ እናውቅበታለን፣ በጋራ ሀገራችን ውስጥ ከፋፋዮን ህወሀት/ወያኔን አሶግደን እናጧጡፈዋለን! እመኑኝ ማለት አያስፈልግም፣ ወያኔ ከሰራው ጥላቻ እጂጉን የሚበልጥ ገለጥ ስናደርግ የምናየው በቂ የፍቅር ስንቅ አለንና፡፡
ጎበዝ እንበርታ! ለራሳችን ነጻነት የምችለውን እናድርግ!!
ድል የህዝብ ነው!
አንድነት ሀይል ነው!!

# Amhara_Resistance� ‪#‎OromoProtest‬ 
�#�EthiopiaProtest�

No comments:

Post a Comment