Monday, August 29, 2016

ሁለት ታላቅ መረጃ በውስጥ ምስመር ደርሶናል!!!


የመጀመሪያው #ከአማራ ክልል
የአማራ ህዝብ በአሁን ሰአት ከወያኔ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ለማላቀቅ በከፍተኛ ሁኔታ በመዋደቅ ላይ ይገኛል። በዚህም ጀግናው የአማራ ህዝብ ጎንደርና ጎጃም ከፊል ሸዋ ላይ ከወያኔ አገዛዝ ነጻ በማስወጣት የራሱን የጎበዝ አለቃ በመሾም ላይ ይገኛል። ይህ ትግል እንደቀጠለ ባለበት ወቅት ቀላል ቁጥር የማይባሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ህዝቡ እየተቀላቀለ የወያኔ አጋዚ ጦር እየተፋለመው ይገኛል። ከአማራ ክልል የተላለፈው መልዕክት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በብዛት ወደ ህዝቡ በሚቀላቀልበት ሰዓት የተወሰኑት መሃል ሰፋሪ ሆነዋል ወደ ህዝብም አንተኩስም ወደ ህዝቡም አንቀላቀልም ያሉ አሉ። ህዝብ ሁልግዜም አሸናፊ ሰለሆነ በአፋጣኝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህዝቡ ጋር ተቀላቅለህ የጠላትን የወያኔ አጋዚ ጦር መድረሻ እንድታሳጣው ታላቅ ጥሪ ከህዝቡ እየተላለፈለት ይገኛል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሆይ አንተ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ጠባቂ እንጅ የጠላት ወያኔ ጠባቂ ስላልሆንክ የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን ታሪክ ሰሪ በመሆን ከህዝብህ ጎን እንድትሰለፍ ህዝብ ጥሪ አቅርቦለሃል። ብዙ የመከላከያ ሰራዊት የህዝቡን ጥሪ በመቀበል ከህዝቡ ጋር እየተቀላቀለ ይገኛል።
ሁለተኛው #ከኦሮሚያ ክልል
በኦሮሚያ ከዳር እስከዳር ሊጠራ ለታቀደው ህዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔዎች ከፍተኛ ፍራቻ ላይ እና ድንጋጤ ላይ እንዳሉ ይታወቃል። ባለስልጣኖችም ቪዛ ለማስመታት በየኤንባሲው በር እየታዩ እንደሆነ ይታወቃል። ይሄ የሚያሳየው በቅርቡ ሁሉም ባለስልጣን አገር ጥለው ለመፈርጠጥ ዝግጅት ላይ ናቸው ማለት ነው።
ይህ በእንድህ እንዳለ በኦሮሚያ ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ትልቅ ወከባ እና ማስገደድ እየተደረገባቸው ነው። ህዝብ ላይ አንተኩስም ብለው አፍ አውጥተው የተናገሩት ሰራዊት የት እንደሚወሰዱም አይታወቁም። ሁሉም ሰራዊት በሚያስብል መልኩ ከህዝብ ጋር እንደሚሰለፍ እያረጋገጠ መሆኑን እና ቀላል ቁጥር የማይባሉ የመከላከያ ሰራዊት ከግዳጅ ቦታ ላይ እየጠፉ እንደሆነ መልዕክት እየደረሰን ነው። የኢትዮጵያ ሰራዊት በሙሉ ከህዝብ ጎን ለመሰለፍ ኦሮሚያ ውስጥ ለግዳጅ ከተሰማራው ከአብዛኛው ሰራዊት የመጣ መረጃ ያመለክታል። የህዝብን ጥሪ በቀበል ከህዝብ ጋር እንደሚሰለፉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የግሌ አስተያየት
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህዝብ ጎን ለመሆን ፈጣን ምላሽ የሰጣችሁ የሰራዊት አባሎች በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ምስጋና በማቅራብ ላይ ይገኛል። የተቀራቹ የመከላከያ ሰራዊት በሙሉ ወሳኝ ግዜና ወቅት ላይ ስለሆንን በፍጥነት የህዝቡን ትግል በመቀላቀል ወንድምህን፣ እህትህን፣ እናትህን፣ አባትህን፣ ብሎም ወድ አገርህን፤ እየገደለ ያለውን ወያኔ በመፋለም ከህዝብህ ጎን በመቆም የተለመደው ጀግና አኩሪ ታሪክህን በመድገም በደማቁ ትጽፈው ዘንድ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አቅርቦለሃል።
ስማ!! ስማ!! የሰማ ላልሰማ ያሰማ !!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ሞት ለገዳይ ወያኔ !!!

No comments:

Post a Comment