Monday, August 22, 2016

የጀግናው አትሌት ሌሊሳ ኦልባና ተቃውሞ በሪዮ ኦሎምፒክ 2016



በኦሎፒክ መድረክ ልዩነት የአለምን ሚዲያ ትኩረት የሳበውን የዘንድሮ ሪዮ ኦሎፒክ ልዩ ክስተት ሆኖ የተገኘው ተወዳዳሪው የብር ተሸላሚ የሌልሳ ዲቢሳ ጉዳይ ነው።
የሚዲያ ሽፋን ለማግኘትና የኢትዮጵያን ጭቆናዊ አገዛዝ ለአለም ለማጋለጥና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግድያ፣ አፈናና ረገጣ ብዙ የተሰራበት እና እየተሰራበት ያለ ጉዳይ ነው፡ በአለም ዙሪያ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ተቀናጅተው የወያኔ አገዛዝ ለአለም ማህበረሰብ እያሳወቁ ባለበት ሰዓት ቢሊዮኖች በሚከታተሉት የአለም ሪዮ ኦሎፒክ ማራቶን ውድድር ላይ እውቁ አትሌት የማይረሳ እና ደማቅ ታሪክ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብሎም በዓለም ማህበረሰብ በመጻፍ የ 2016 ጀግና አትሌት ብቻ ሳይሆን ጀግና የህዝብ አለኝታ መሆኑን በማሳየት ወደ መጨረሻው ደቂቃዎች ውስጥ እጁን በተደጋጋሚ በማጣመር ወያኔን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ኢሰባዊ ድርጊት በማውገዝ ከህዝብ ጎን መቆሙን አረጋግጣል።
የወያኔን ገመና በአለም ማህበረሰብ ውስጥ በኦሎፒኩ ሜዳ ላይ አስጥቶታል። የኢትዮጵያን ጭቆናዊ አገዛዝ እና በደል ለአለም ማህበረሰብ ከማሳወቁ አልፎ የአለም ሚዲያዎችን አጨናንቆ ውሎአል አሁንም ሌሊሳ የአለምን ህዝብ ትኩረት የሳበ ብቻ ሳይሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አይነት ግፍ እንዳለ ያሳወቀ ጀግና ነው።
የእስፖርቱ ዓለም አርበኛ ጀግናው አትሌት ሌሊሳ ኦልባና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እንዲሁም የኢትዮጵያዊያን ኩራትና ክብራችን ነህ ሁሌም እናስባለን እናከብርሃለን ፤
የአለም ሚዲያዎችም የጃግናው አትሌት ሌሊሳ ኦልባና ተቃውሞውን እንዲህ ተቀባብለው ዘግበውታል።

መርጋ ደጀኔ

No comments:

Post a Comment