በገዢው ሥርዓት ህወሓት-ኢህአዴግ የተገደሉ ንፁሐን ዜጎችን ለማሰብ ብሔራዊ የኀዘን ጥሪ ያቀረቡት በቂሊንጦ የሚገኙ በዞን 1 ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ጨለማ ቤት መወርወራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ገለጹ::
ጥሪውን በዋናነት ያቀረቡት በዞን 4 የሚገኙት 9 የፖለቲካ እስረኞች(በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ አበበ ኡርጌሳ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ) ቅጣት ቤት ይገኛሉ::
እስረኞቹ ፀጉራቸውን መላጨታቸው የታወቀ ሲሆን በቅርቡ የእስረኞች ልብስ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ቱታ እንዲለብሱ ግዴታ በመጣሉ ጥቁር ልብስ መልበስ እንዳልቻሉ ኢሳት ለመርዳት ችሏል:: ሆኖም በዞን 1 ያሉት እስረኞች ጥቁር ለብሰው በመታየታቸው ጨለማ ክፍል እንዲገቡ ተደርጓል::
የእስረኞቹን ጥሪ በመስማት በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችና በመንግሥት ተገፍተው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ጥቁሩ ለብሰው ፀጉራቸውን ተላጭተው በግፍ የተገደሉ ወገኖቻቸውን አስበዋል::
በተያያዘ የእስርቤት ዜና የ እስርቤት የሌሊት ጠባቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው መሰወራቸው እየተነገረ ነው። ሁኔታው በመንግሥት ላይ ድንጋጤ ፈጥሮ በእስር ቤቱ ዙሪያ ግርግር እንደነበር ተገልጿል::ኢሳት ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረገ ይገኛል::በዚህ ዓመት ብቻ በጠባቂዎች ተመሳሳይ እርምጃ ሲወሰድ ለ3ኛ ጌዜ ነው::
No comments:
Post a Comment