Sunday, August 28, 2016

Abebe Gellaw ቅኝ አንገዛም!


እራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ብሎ የሚጠራው ዘራፊና ፋሺስታዊ ቡድን እንደ ነጋበት ጅብ መግቢያና መፈናፈኛ እያጣ ነው። 
ህወሃት አላማዬን አሳክቻለሁ ትግራይን ነጻ አውጥቻለሁ እያለ ቢያቅራራም ከመረብ ባሻገር ያለውን ህዝብና አገር ልክ እንደ ቅኝ ገዢ እየዘረፈ፣ በግፍ እየገደለና እያሰቃየ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል። ህወሃት አላማው ትግራይን ነጻ ማውጣት ስለሆነ (ከማን ነጻ እንደሚያወጣ ባይታወቅም) ከትግራይ ባሻገር መሬት መቀማት፣ ማስገበር፣ አድሏዊ ስርአት ማንሰራፋት፣ መጠነ ሰፊ ዘረፋ ማካሄድ፣ መግደል፣ በዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ሰቆቃ መፈጸም፣ ህዝብ ማፈናቀል፣ መከፋፈል እና በዘረኝነት ህዝቦችን መፈረጅ አይነተኛ ባህሪያቶቹ ናቸው። 
ህወሃት ገና ሲፈጠር ገንጣይና አስገንጣይ ስለሆነ ህዝቡ ከፈቀደ ትግራይን መገንጠል ይችላል። እንደውም እውነቱን ለመናገር ትግራይ በአሁኑ ግዜ ሙሉ በሙሉ የህወሃት እርስት መሆኗ ግልጽ ነው። ያለህወሃት በትግራይ ላይ ማንም አያዝም። በቅርቡም ሳሞራ ዩኑስ ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ የለም ብሎናል። ይሁንና የትግራይ ህዝብ አገሩን አጥቶ ብቻውን በህወሃት ፋሺስታዊ አገዛዝ ስር ይቀጥላል ብሎ ማመን ይከብዳል። ፈቃዱ ከሆነ ግን ማንም ሊያስቆመው አይገባም።
ህወሃት በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በነጻነትና በእኩልነት ስም የጫነው ፋሺስታዊ ቅኝ አገዝ ጭቁኑ ህዝብ በቃኝ ብሏል። በየአደባባዩ አሻፈረኝ ብሎ የተነሳው ህዝብ "ጠባቡና ትምክተኛው የትግራይ ነጻ አውጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይሰራል?" ህወሃት እስከመቼ የኢትዮጵያን ህዝብ ደም ይመጣል? እስከ መቼስ እየገደለና እየዘረፈ መቀጠል ይችላል? የሚል መሰረታዊ ጥያቄ እያነሳ ነው። የህወሃት ቅኝ አገዛዝ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የጸረ ቅኝ አገዛዝ ተግሉ በመላው ኢትዮጵያ ይፋፋም። ህዝቡ ግብር መክፈል ያቁም። በህወሃትና በቅጥረኞቹ የንግድ ተቋማት ላይ መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ማእቀብ ይደረግ።

No comments:

Post a Comment