Friday, August 19, 2016

አትነሳም ወይ !! አትነሳም ወይ ለነፃነት አትነሳም ወይ ለፍትህ አትነሳም ወይ ለእኩልነት አትነሳም ወይ ለሐይማኖትህ አንገት ደፍቶ መኖር አይበቃህም ወይ ይበቃል ይበቃል ይበቃል ተርቦ ተጠምቶ አልቅሶ ተጠቅቶ በርሃብ በእርዛት በህመም በችግር እየተንገላቱ ዘላለም ከመኖር ከእኩልነትና ከነፃነት ጋራ ይሻላል መቃብር ፋም ይዞ እሳት ነዶ ጋ ብሎ ይሞቃል ብድሩ እስኪደርሰው ሰው በሰው ይስቃል ቆስቁሰው ቆስቁስው ያቃጠሉት ክምር ብቻውን አይነድም ቆስቋሹን ሳይጨምር እነአምበስ ሲተኙ ታሪክ አስጠፍተው የአባቶች አደራ ክብር አስደፍረው ተንቀው ተዋርደው አረንቋ ተጥለው ጥቃትን ለምደውት ይሁን አሜን ብለው ተኙ ተኙ ተኙ እንደምን ተሞኙ እንረስ ካላችሁ ተስማምተን እንረስ እንተወው ካላችሁ ተዉት ዳዋ ይልበስ የናንተ ፈርሶ ነው የኛ ቤት የሚፈርስ የናንተ ፈርሶ ነው የኛ ቤት የሚፈርስ ባጥፈው ደነዘዘኝ ምላሴን እንደ እግር ለካ ነፃነት ነው እንዳሻው ሚያናግር ሄደ ንጉስ ሄደ ጎራውን አለፈው ድንጉሉ ቀረ እንጅ የማይናደፈው ************************* እንኳን ከውርደት ጋር እንኳን ከችግር ጋር እንኳን ከስደት ጋር ከደዌ ከጥቃት ከክብር ጋር ቢሆን ከብዙ ጌትነት ኑሮ ጣዕም የለውም ህሊና አይገዘትም ከሌለ ነፃነት *********** እንደ ስሜት ክፉ አይቶ እንዳለማየት የሞት የበኸር ልጅ ከወለደች ጥቃት በአንድነት ባይቆሙ ገጥሞ ትከሻቸው የደንገል ወጋግራ የድል አውታር ሆነው በመካከላቸው ንፋስ እየገባ ያንጓልላቸዋል አውነት ስንገነባ ኮረም አለማጣ ምነው ዝንብ ወረረው ራያና አዘቦ ምነው ዝንብ ወረረው ወይ ሰቲት ሁመራን ምነው ዝንብ ወረረው ወልቃይት ጠገዴን ምነው ዝንብ ወረረው አልፎ ሚከለክል ጌታ እንዳልነበረው ባጥፈው ደነዘዘኝ ምላሴን እንደ እግር ለካ ነፃነት ነው እንዳሻው ሚያናግር ሄደ ንጉስ ሄደ ጎራውን አለፈው ድንጉሉ ቀረ እንጅ የማይናደፈው **አትነሳም ወይ !!** **አዲስ የትግል ቀስቃሽ ዘፈን**Ethio Patriots Atenesam Woy 2016

No comments:

Post a Comment