Tuesday, August 23, 2016

እለታዊ መረጃ ከኢሳት


-በባህርዳር አድማውን ለ3ኛ ቀን ቀጥሎአል። አድማው በቆላ ድባ፣ ጯሂትና ጎርጎራም በመካሄድ ላይ ነው።

-የአማራ ክልል የደህንነት አባላት “ ወያኔ ዘመኑ አልቋል” ይላሉ። ከእንግዲህ እንደልባችሁ ተናገሩ በማለት ሲናገሩ ተሰምቷል።
- በጎንደር ከተማ ተመሳሳይ የስራ ማቆም አድማና የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ ለ2ኛ ጊዜ ሊደረግ ነው
-በደብረማርቆስ ወንድሟን ለመያዝ ከመጡት የፈደራል ፖሊሶች መካከል አንዱን አናቱን ብላ ለሆስፒታል የዳረገቸው ሴት በአካባቢው ህዝብ እንደጀግና ስትቆጠር፣ ፖሊሱ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።

- -የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያጸደቀው “ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውሶችን ለመከላከል የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ የማሽቆልቆል ምዕራፍ ተዘግቶ የእድገት ምዕራፍ የተከፈተበት የሩብ ምዕተ ዓመት የትግልና የድል ጉዞ” የሚል ርእስ ያለው ሰነድ ደርሶናል። በሰነዱ ላይ ከሰፈሩት ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
“በራሳችን ድክመቶች የተነሳ የተከማቹ ሌሎች አሉታዊ አቅሞችም /Negative Critical Mass/ አሏቸው፡፡እነዚህም መንግስትን እስከመገልበጥ ደረጃ የመድረስ አቅም አላቸው፡፡”

“ባለፈው ሩብ ምዕተ ዓመት በተካሄደው ትግል የተገኘውን ውጤት በአጭሩ ለመግለፅ ቢፈለግ "በአንድ በኩል በጣም ተስፋ ያላትና የምታጓጓ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ስጋት የሚታዩ ችግሮችና ፈተናዎች ያሉባት አገር ፈጥረናል" ብሎ ማጠቃለል ይቻላል፡፡ የሥራችን ፍሬ የሆነው መልካም ነገር ሁሉ የሚያጓጓውንና የሚያሳሳውን እውነታና ተስፋ ያሳያል፡፡ በድክመታችን ምክንያት የተፈጠረው የጥፋት እውነታ ደግሞ አሳሳቢውን እውነታ ያመላክታል፡፡ ህዝቡን በቁስ ለማሳደግ በተደረገው ጥረት ጥቂት ምንጫቸው ያልታወቁ ሚልየነሮችን ፈጥረናል፡፡ የቁስ ልማት አካሂደናል፡፡ የብሄር መከፋፈሎች ደግሚ የስርዓቱ አደጋ መሆናቸው ተገልፆልናል፡፡”
“አገሪቱ አዲስ ሀብት ሊፈጠርባት የምትችል አገር እንዳትሆን በማድረጋቸው ብዙኀኑ ህዝብ ለድህነትና የበይ ተመልካችነት ተዳርጎ ኖሯል፡፡ በዚህ ላይ የህግ የበላይነት የጠፋበት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት፣ ህዝብን በቅልጥፍናና በውጤታማነት ማገልገል የማይታወቅበት ዘመን ስለነበር፣ አገሪቱና ህዝቦቿ ቀስ በቀስ በመልካም አስተዳደር እጦት ለውድቀት የሚዳረጉበት እድልና ሁኔታ እጅጉን ሰፍቶ ነበር፡፡ ይህን የመሰለው በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ አሁን ባለው የኢህአደግ የአገዛዝ ዘመንም እንደቀጠለ ነው፡፡”

No comments:

Post a Comment