Wednesday, August 24, 2016

ፈሲል የኔዓለም :



በርካታ የሰሜን ጎንደር እና የምእራብ ጎጃም ከተሞች 
ራሳቸውን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ እያወጡ ነው። ይህን ድል እንዴት መጠበቅና ማጠናከር ( consolidate) ይቻላል የሚለው ፈታኝ ጥያቄ ነው። የተፈጠረውን የስልጣን ክፍተት ( power vacuum) ለመሙላት የሚያስችል አፋጣኝ ተተኪ ሃይል እስኪመጣ ፣ ድሉ ሊቀለበስ ይችላልና ውይይት ማድረጉ ይበጃል። ሁሉም ሰው አላስፈላጊ በሆኑ የጎንዮሽ ጉዳዮች ላይ ከመነታረክ የአዕምሮ ጉልበቱንና ጊዜውን በዚህ ላይ አድርጎ ቢመካከር መልካም ነውና ሃሳብ ያላችሁ ሃሳባችሁን ወርውሩ። መሬት ላይ ለነጻነቱ እየተፋለመ ያለው ህዝብ ከልጆቹ ብዙ ይጠብቃል። ይህ በብዙ የደም መስዋትነት የተገኘው ድል በፍጹም እንዲቀለበስ አይፈልግምና እንመካከር።

No comments:

Post a Comment