Sunday, August 28, 2016

Patriotic Ginbot 7


የወያኔን ዘረኛና አድሎአዊ አገዛዝ በቃን በማለት በመላው የሀገራችን ክፍል የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድማሱን እያሰፋ መዳረሻውን ነጻነት ፤ ፍትህ ፤ እኩልነት እና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ይገኛል። ይህንንም የነጻነት ትግል ከግብ ለማድረስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብርና አስተዋጽዖ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም። የሕውዓት ዘረኛ አገዛዝ በ25 ዓመት የአገዛዝ ዘመኑ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሕዝብን ከሕዝብ በሀይማኖት ፤ በበብሄርና በጎሳ በማለያየት ለማጋጨት ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልወጣው አቀበት አልነበረም ። ነገርግን አርቆ አስተዋዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ይህንን ዘረኛና ከፋፋይ አምባገነን አገዛዝ በቃን ወግድልን በማለት በማንነቱ ሳይለያይ ከጫፍ እስከ ጫፍ አንድ አይነት ድምጽ በማሰማት የዘረኞችን አገዛዝ አስወግዶ ነጻነቱን በዕጁ ለማስገባት ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል። 
ይሁንና የወያኔው አገዛዝ እጁ ረዥም በመሆኑ ሰላዮቹን እና አንዳንድ ከህሊናቸው ይልቅ ሆዳቸው የቀደመባቸውን ደካሞች በማሰባሰብ የተጀመረውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ በማሳት ከተቻለ የአገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም ካልሆነም ወዳላስፈላጊ እርስ በርስ ግጭት እንዲያመራ ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ ይገኛል። 
በመሆኑም የተጀመረው የህልውናና የነጻነት ትግል ከብሄርተኝነት ወይም ከጎሳ ይልቅ ሰብዓዊነትን ያሥቀደመና ለአብሮነታችን ጽኑ መሰረት የሚጥል ሐገራዊ ፋይዳ የሚኖረው ይሆን ዘንድ ትንቅንቁ ከሕውዓት አገዛዝ ጋር ብቻ ሳይሆን ሕውዓት ላለፉት 25 አመታት ከዘራው የዘረኝነት አስተሳሰብ ጭምር ጋር መሆን ይኖርበታል።
ሰላም ፤ ፍትሕ ፤ ዴሞክራሲ እና እኩልነት የሰፈነባት የሁላችንም የሆነች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ዘረኝነትን ወይም የብሄርተኝነት አስተሳሰብን ልንጸየፈው ይገባል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

No comments:

Post a Comment