Sunday, May 28, 2017

የኢትዮጵያ ገዥ ቡድን ሰፊ የእርሻ መሬት ለሱዳን ለማስረከብ ዝግጅት መጨረሱ ታወቀ


የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ሓሙስና ቅዳሜ ይከታተሉ
የዕለተ እሁድ ግንቦት -20 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Saturday, May 27, 2017

የኢትዮጵያ አገር አድን ጉባኤ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ጁን 17፣ 2017


የኢትዮጵያን ህዝቦች የነጻነት ትግል በአንድ አገራዊ ጥላ ስር አስተባብሮ ለዲሞክራሲ ሽግግር በማዘጋጀት በአራት ድርጅቶች የጋራ ስምምነት የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ተልዕኮ እና ራዕውን ለህዝቡ ለማስተዋወቅ ከህዝቡ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ለመመለስና ብሎም ትግሉን አጠናክሮ ለግብ ለማብቃት የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ/DCESON/ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በጋራ በኖርዌይ እና በአካባቢው ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ ጋር ለመወያየት ! ጉባኤ አዘጋጅቶል።
በቦታው በክብር እንግድነት ተጋባዥ የንቅናቄው የመማክርት ጉባኤ ተባባሪ ሊቀመንበር የሆኑት አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የመማክርት ጉባኤ አባል አቶ ሌንጮ ለታ...... እርሰወም በዚህ ፕሮግራም ላይ በመገኘት እንዲሁም ሌሎችንም በመጋበዝ ታሪካዊና ወቅታዊ አገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ቀን ፣ ጁን 17- 2017
ሰዓት ፣ 15 00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ ፣ በቅርቡ ይገለጻል
አዘጋጅ ፣የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርዌይ
መረጃ ፣ 94254599 .....46240132
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!

Friday, May 26, 2017

ኢትዮጵያና ሱዳን በድበር ጉዳይ ጎንደር ውስጥ ስብሰባ መቀመጣቸው ታወቀ


የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ሓሙስና ቅዳሜ ይከታተሉ
የዕለተ አርብ ግንቦት -18 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Thursday, May 25, 2017

በአገሪቱ ያሉ የደህንነት ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው


የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ሓሙስና ቅዳሜ ይከታተሉ
የዕለተ ሓሙስ ግንቦት -17- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Wednesday, May 24, 2017

የስፓርት ሜዳዎች ለሕዝባዊ ትግል መፋፋም አገልግሎት ይዋሉ!

May 24, 2017
የህወሓት አገዛዝን በመሰለ አፋኝ ሥርዓት የሚገኝ ሕዝብ ለተቃውሞ መግለጫነት የሚያገለግሉ አጋጣሚዎችን ሁሉ መጠቀሙ ብልህነት ነው። ብሔራዊ፣ ባህላዊና የሀይማኖት በዓላት፤ የሙዚቃ ድግሶች፤ የስፓርት ሜዳዎች፤ ትምህርት ቤቶችና ገበያዎች ለተቃውሞ መነሻነት ምቹ ናቸው። እነዚህን ሁሉ በአግባቡ መጠቀም ለሁለገብ ትግል ውጤታማነትና ሕዝብን ለማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አላቸው።

በተለይ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች በርካታ ሕዝብ በጠባብ ቦታ የሚሰበሰብባቸው በመሆኑ፤ አብዛኛው ተመልካችም በእድሜ ወጣትና ንቁ ስለሆነ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ለመቀስቀስ የተመቹ ቦታዎች ናቸው። በአገራችን በኢትዮጵያ ሁኔታ ግን በእስከ ዛሬ ልምድ የእግር ኳስ ሜዳዎቻችን በዚህ ረገድ ያበረከቱት አስተዋጽዖ እጅግ አነስተኛ ነው። የእግር ኳስ ሜዳዎቻችን የሕዝብ ብሶት መግለጫ ከመሆን ይልቅ አፋኙ ሥርዓት የሚያሰራጫቸው ዘርና አካባቢን መሠረት ያደረጉ ልዩነቶችን ማራገቢያ ሲሆኑ ይስተዋላል።

Tuesday, May 23, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ ማስመረቁ ታወቀ፡፡


(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
********************************
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች በወታደራዊ፣ በፖለቲካ፣ በእጅበእጅ (ቴኳንዶ)፣ በመረጃና ደህንነት እንዲሁም በጉሬላ ውጊያ ለበርካታ ወራት ሲያሰለጥናቸው ቆይቶ እሁድ ግንቦት 13 ቀን 2009 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁ ታውቋል፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ና ከተለያዩ ግንባሮች የመጡ አርበኛ ታጋዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል ፡፡
የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ምክትል ሃላፊ የሆኑት አርበኛ ታጋይ ካሳሁን ይነሱም አሁን ወቅቱ ህዝቡ በአንድነት ሆ ብሎ የተነሳበትና ከምንም ጊዜ በላይ ህዝብ አርበኞች ግንቦት 7ትን የሚጠብቅበት ጊዜ ላይ ነው የምንገኘው ፡፡ በዚህ ጊዜ ለዚህ ትግል የቻላችሁትን ሁሉ አስተዋፅዎ ለማድረግ በቁርጠኝነት በመነሳታችሁና ለህዝብ አለኝታ ለመሆን የሚጠበቅባችሁን ስልጠና በአግባቡ በመወጣታችሁና ይህን አድካሚ ስልጠና ጨርሳችሁ ለዛሬ ለምርቃት ቀናችሁ በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ ማስመረቁ ታወቀ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ሓሙስና ቅዳሜ ይከታተሉ
የዕለተ ማክሰኞ ግንቦት -15- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት
http://www.patriotg7.org/wp-content/uploads/2017/05/Ag7-Radio.23.05.2017.mp3

Monday, May 22, 2017

የአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት በህዝባችን ላይ የተፈጸመውን ወንጀል መሸፈኛ ሊሆን አይችልም! May 20, 2017

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ድርጅትና እንደ መንግሥት በአገራችን ውስጥ እንዲተገበሩ በወጡ አፋኝ ፖሊሲዎችና በህዝባችን ላይ በተወሰዱ ፋሽስታዊ እርምጃዎች ሁሉ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ጥቂት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ቴዎድሮስ አድሃኖም አንዱ ነው።

ይህ ወንጀለኛ ግለሰብ የአምባገነኖች ስብስብ በሆነው የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት እጩ ሆኖ ሲወጣ እንደ ትልቅ ገድል የተቆጠረለት የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ሆኖ ባገለገለባቸው አመታት አስመዝግቧል የተባለው የጤና መሻሻልና በውጪ ጉዳይ ሚንስትርነት አበርክቷል የተባሉት አስተዋጾዎች ናቸው።
ምዕራባዊያን ለጋሾች ለታዳጊ አገራት የጤና አገልግሎት በየአመቱ የሚሰጡትን ገንዘብ የሚ

የኢትዮጵያ አገር አድን ጉባኤ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ

ኑ !! የጋራችን ጉዳይ በሆነው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንምከር !
በአሁን ወቅት አገራችን የገጠማት አገዛዝ ደግሞ ከተለመደው የአባገንነት ሸክም በተጨማሪ ኢትዮጵያን በቅኝ ሊገዛት እንደሞከረው ጣሊያን ህዝባችንን በየፈርጁ በዘር ከፋፍሎ በመግዛት የሀገራችንንና የህብረተሰባችንን ህልውና ጭምር የሚፈታተን ሆናል በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለነጻነትና ዲሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርጉትን ትግል እጅግ ወሳኝ ደረጃ በመድረሱ የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ/DCESON/ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በጋራ በኖርዌይ ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ ጋር ለመወያየት ! ጉባኤ አዘጋጅቶል። በቦታው በክብር እንግድነት ተጋባዥ የንቅናቄው የመማክርት ጉባኤ ተባባሪ ሊቀመንበር የሆኑት አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የመማክርት ጉባኤ አባል አቶ ሌንጮ ለታ...... እርሰወም በዚህ ፕሮግራም ላይ በመገኘት እንዲሁም ሌሎችንም በመጋበዝ ታሪካዊና ወቅታዊ አገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ቀን ፣ ጁን 17- 2017
ሰዓት ፣ 15 00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ ፣ በቅርቡ ይገለጻል
አዘጋጅ ፣የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርዌይ
መረጃ ፣ 94254599 .....46240132
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!

Saturday, May 20, 2017

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባት (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባት (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባት (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 በጋራ ለመስራት ተስማሙ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች በጋራ ለመታገልና ከሌሎች የኢትዮጵያ የለውጥ ሃይላት ጋር ለመተባበር መስማማታቸውን ድርጅቶቹ ጀርመን ፍራንክፈርት ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል። 

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 እኤአ ከሜይ 15 እስከ ሜይ 17 በጀርመን ፍራንክፈርት ለሶስት ቀናት ተወያይተው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት መገምገማቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።
ስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ በሃገሪቱ ከፍተኛ ቀውስ ፈጥሯል በማለት በጋራ መግለጫቸው ያወጡት ሁለቱ ድርጅቶች፣ ይህ አስጊ ሁኔታ በፍጥነት ካልተቀለበሰ ሰብዓዊና ፖለቲካዊ ቀውስ በኢትዮጵያና በአካባቢው እንደሚፈጠር ያላቸውንም ስጋት ገልጸዋል። ይህንን ስጋት ለማስወገድ በጥልቀት መምከራቸውንና በጋራ ለመታገል መወሰናቸውንም አስታውቀዋል።
የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ እንዲወገድና የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ እንዲያበቃል በግንባር ቀደምትነት መሰለፋቸውን የገለጹት ኦብነግና አርበኞች ግንቦት 7 ለሌሎች የዴሞክራሲ ሃይሎችም ጥሪ አቅርበዋል። ተመጣጣኝ ውክልና ወደ አለበት ሃቀኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችሉ መሰረቶችን በጋራ መኖራቸውንም በመግለጫቸው ፈንጥቀዋል።

የአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት በህዝባችን ላይ የተፈጸመውን ወንጀል መሸፈኛ ሊሆን አይችልም! May 20, 2017

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ድርጅትና እንደ መንግሥት በአገራችን ውስጥ እንዲተገበሩ በወጡ አፋኝ ፖሊሲዎችና በህዝባችን ላይ በተወሰዱ ፋሽስታዊ እርምጃዎች ሁሉ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ጥቂት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ቴዎድሮስ አድሃኖም አንዱ ነው።
ይህ ወንጀለኛ ግለሰብ የአምባገነኖች ስብስብ በሆነው የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት እጩ ሆኖ ሲወጣ እንደ ትልቅ ገድል የተቆጠረለት የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ሆኖ ባገለገለባቸው አመታት አስመዝግቧል የተባለው የጤና መሻሻልና በውጪ ጉዳይ ሚንስትርነት አበርክቷል የተባሉት አስተዋጾዎች ናቸው።

Thursday, May 18, 2017

አርበኞች ግንቦት7 እና ኦብነግ በጋራ ለመታገል ተስማሙ

የአርበኞች ግንቦት7 የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄና የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት9 ቀን 2009 ዓም በፍራንክፈርት ከተማ፣ በሁለቱም ድርጅቶች ተወካዮች አማካኝነት ባደረጉት ስብሰባ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝና የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃና ስቃይ እንዲያበቃ በጋራ ለመታገል፣ ሌሎች ዲሞክራሲ ሃይሎችን በማሳተፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሃይል እንዲያገኝ በግንባር ቀደምትነት ለመታገል ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ፈጸመ


የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ሓሙስና ቅዳሜ ይከታተሉ
የዕለተ - ሓሙስ - ግንቦት -10- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Friday, May 5, 2017

Tedros lied and people died in Ethiopia Cholera outbreak 2008. #No Tedros Adhanom for WHO #WHO #UN


Tedros refused international emergency medical aid and people died in Cholera outbreak of 2008 #No Tedros Adhanom for WHO #WHO #UN #BBC
Tedros Adhanom, no integrity, no competency, no morality, unethical will sacrifice World health on the 12th day to corporate firms #WHO #UN
Tedros took away the rights of women in Amhara Region the God given right to have a baby, tantamount to gradual ethnic cleansing #WHO #UN #Genocide Watch

Tedros denied women in Amhara Region the God given right to have a baby, tantamount to gradual ethnic cleansing #WHO #UN #Genocide Watch
Tedros used health policy to reduce population of one Ethnic group, tantamount to ethnic cleansing #No Tedros Adhanom for WHO #WHO #Genocide Watch
Africa think again! Do not reward corrupt Tedros who uses health service as a political weapon with the ultimate humanitarian role #WHO #UN
@Metasebia Ketsela