Tuesday, May 23, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ ማስመረቁ ታወቀ፡፡


(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
********************************
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች በወታደራዊ፣ በፖለቲካ፣ በእጅበእጅ (ቴኳንዶ)፣ በመረጃና ደህንነት እንዲሁም በጉሬላ ውጊያ ለበርካታ ወራት ሲያሰለጥናቸው ቆይቶ እሁድ ግንቦት 13 ቀን 2009 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁ ታውቋል፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ና ከተለያዩ ግንባሮች የመጡ አርበኛ ታጋዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል ፡፡
የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ምክትል ሃላፊ የሆኑት አርበኛ ታጋይ ካሳሁን ይነሱም አሁን ወቅቱ ህዝቡ በአንድነት ሆ ብሎ የተነሳበትና ከምንም ጊዜ በላይ ህዝብ አርበኞች ግንቦት 7ትን የሚጠብቅበት ጊዜ ላይ ነው የምንገኘው ፡፡ በዚህ ጊዜ ለዚህ ትግል የቻላችሁትን ሁሉ አስተዋፅዎ ለማድረግ በቁርጠኝነት በመነሳታችሁና ለህዝብ አለኝታ ለመሆን የሚጠበቅባችሁን ስልጠና በአግባቡ በመወጣታችሁና ይህን አድካሚ ስልጠና ጨርሳችሁ ለዛሬ ለምርቃት ቀናችሁ በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

No comments:

Post a Comment