Wednesday, December 2, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


በጎንደር ከተማ በትናንትናው ዕለት በደረሰው የህወሓት ግዙፍ ወህኒ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት በህወሓት መከላከያ ሰራዊት በተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የሞቱ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ በታማኝ ምንጮች ተረጋግጧል፡፡ ከተጨፈጨፉት እልፍ አዕላፍ ወገኖቻችን መካከል ማንነታቸው የተለየው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ትናንትና ማክሰኞ ዕለት ህዳር 21 2008 ዓ.ም በጎንደሩ የህወሓት ግዙፍ ወህኒ /ባህታ እስር ቤት/ የተነሳው ከባድ የእሳት ቃጠሎ የጀመረው ከረፋዱ ወደ አራት ሰዓት ገደማ ነው፡፡ በመሆኑም የህወሓት አገዛዝ ታማኝ ጦሩን ከሁመራና አካባቢው ጭኖ በፍጥነት ወደ ጎንደር ከተማ በማጓጓዝ እስረኞችንና ሰላማዊ ነዋሪዎችን በጥይት ጨፍጭፏቸዋል፡፡ የተጨፈጨፉት ሰዎች ቁጥራቸው የትየለሌ እንደሆነና ከመጠን በላይ የሆነ አስከሬን በአንድ ላይ ተከማችቶ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል፡፡
ከተጨፈጨፉት እጅግ በጣም በርካታ ሰዎች መካከል ማንነታቸው የተለዩት ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ሲፈፀም ውሏል፡፡ አቶ አዱኛ የተባለው ሟች ዛሬ ከሰዓት በፊት በወገራ ወረዳ ገደብዬ ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተቀብሯል፡፡
የጎንደር ህዝብ በህወሓት አገዛዝ ላይ ከመቸውም ጊዜ በላይ ጥርሱን ነግሷል፡፡ ስለሆነም በጎንደርና አካባቢው ከፍተኛ ውጥረት አይሏል፡፡

Prof. Berhanu Nega talks about his EU discussion on VOA

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለአውሮፓ ፓርላማ መድረክ ከተናገሩት

''የኢትይዮጵያ ህዝብ በህወሀት ስርዓት ተንገሽግሿል። ከልክ ባለፈ ተሰላችቷል። ለለውጥ ተነስቷል። በየቦታው የነጻነት ጥማቱ ወደ ተግባር እየተሸጋገረ ነው። ነገ ውጤቱን ታዩ ታላችሁ።" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለአውሮፓ ፓርላማ መድረክ ከተናገሩት

Tuesday, December 1, 2015

Prof. Berhanu Nega in Brussels, EU meeting (ESAT News)

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዛሬዉ የአዉሮፓ ሕብረት ንግግራቸዉ – VOA - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48655#sthash.tv4u0rPt.dpuf

(negaVOA Amharic) የአርበኞት ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ብረስልስ ቤልጄም በሚገኘዉ የአዉሮፓ ፓርላማ በኢትዮጽያ ስለተከሰተዉ ድርቅና ረሃብ ማብራሪያ መስጠታቸዉ ታዉቋል። ዋሽንግተን ዲሲ — የኢትዮጵያን መንግሥት በትጥቅ ከሥልጣን የማዉረድ ዓላማ ያነገበዉን ግንቦት ሰባት በመምራት በጎሬቤት ኤርትራ እንደሚገኙ የሚታወቀዉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ስብሰባዉን ባዘጋጁት የፓርላማዉ አባላት እንደተጋበዙ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አሁን በድርቅ ምክንያት ስለተከሰተዉ የምግብ እጥረት ያደረጉት ንግግርም ድርቅ ተፈጥሮአዊ ክስተት፣ ረሃብ ግን የመንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዉድቀት መሆኑን የሚያመለክት ነዉ ብለዋል። “ከኢትዮጵያ ረሃብን ማስወገድ ከባድ አይደለም” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፤ መንግሥት ሁሉን ነገር የመቆጣጠር አባዜ ይዞታል፣ገበሬዉን መፈናፈኛ አሳጥቶ ከእለት ጉርስ ያለፈ የኢኮኖሚ ሕይወት እንዳይኖረዉ አድጓል” ብለዋል፡፡ አያይዘውም እየጨመረ የሄደዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛትና እንዲሁም ፤ ኬሚካል ማዳበሪያ እየፈጠረ ያለዉ ችግር እንደ ምግብ እጥረት ምክንያትነት ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአሁኑን ድርቅ ኢልኒኖ የተባለዉ የአየር መዛባት እንዳስከተለዉና እስካሁን ድርቁ ባሰከተለዉ ረሃብ የሞተ ሰዉ እንደሌለ ለአስቸኳይ ጊዜ የመደበዉን ርዳታም ድርቅ ላጠቃዉ ሕዝብ እያደለ መሆኑን ይናገራል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዛሬዉ የአዉሮፓ ሕብረት ንግግራቸዉ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካ ጉዳዮችም ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለለዉጥ አሻፈረኝ በማለት ተቃዋሚዎች ጋር የገባዉ ፍጥጫ ለአዉሮፓ ሕብረት አሳሳቢ በመሆኑ አባላቱ ሰለ ወቅታዊ የአገሪቱ የፓለቲካ ሁኔታም እንደተወያዩ ተናግረዋል። ቃለ-ምልልሱን ለመስማት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48655#sthash.tv4u0rPt.dpuf

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


‪#‎የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ከህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊትና ልዩ ኃይል ጦር ጋር ዋልድባ ላይ ባደረገው ከባድ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡
=========================================================
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ዛሬ ከቀትር በኋላ ዋልድባ ላይ በሰነዘረው ድንገተኛ እና ከባድ ጥቃት የህወሓት መራሹን የመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ኃይል ጦር ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት ድረስ ለሁለት ተከታታይ ሰዓታት በጥይት ቆልቶታል፡፡

በመሆኑም ከህወሓት ጦር በኩል በትንሹ 29 ወታደሮች ሲሞቱ ከ40 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፡

 
ከመርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)
ኢትዮጵያ ነጻነቷን የምታገኝበት ግዜ መቷል የወያኔ ሹማምንቶች የዘረፉትን የህዝብ ሃብት በማሸሽ ላይ ናቸው። ወደ ቻይና እና ወደ አረብ አገራት ለመደበቅ የመጨረሻውን ዝግጅት እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አገርህን ነቅተህ ጠብቅ።
እውነቱ መቼም ቢሆን እውነት ነው ትቀጥን ይሆናል እንጂ አትበጠስም ትደክም ይሆናል  እንጂ  አትጠፋም አሁን የኢትዮጵያ ሁለት ምርጫ ተዘጋጅቶላታል ለእውነትና ለህዝብ ማደር አልያም ለሆድና ለውሸት አባት ለወያኔ ማደር።