Tuesday, December 1, 2015

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፡

 
ከመርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)
ኢትዮጵያ ነጻነቷን የምታገኝበት ግዜ መቷል የወያኔ ሹማምንቶች የዘረፉትን የህዝብ ሃብት በማሸሽ ላይ ናቸው። ወደ ቻይና እና ወደ አረብ አገራት ለመደበቅ የመጨረሻውን ዝግጅት እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አገርህን ነቅተህ ጠብቅ።
እውነቱ መቼም ቢሆን እውነት ነው ትቀጥን ይሆናል እንጂ አትበጠስም ትደክም ይሆናል  እንጂ  አትጠፋም አሁን የኢትዮጵያ ሁለት ምርጫ ተዘጋጅቶላታል ለእውነትና ለህዝብ ማደር አልያም ለሆድና ለውሸት አባት ለወያኔ ማደር።

 መቼም ከዚህ ቀደም ባሉት ግዚያቶች ሞላ አስገደም ከዳ ተብሎ በወያኔ ሚዲያዎች ሱፍ አልብሰውት የተነገረውን ብቻ እየተደናበረ ሲናገር ተመልክተነዋል። በአገር ቤት ሚዲያዎች ትልቅ የሚዲያ ሽፋን ተሰጥቶት ሲተረክለት ነበር። አሁን እሱን የውሸት ቅንብር  ልደግምላችሁ አይደለም እንደዚህ አይነቱን ሆድ የሚነፉ የቅሌት ቅንብር 25 ዓመት ሙሉ ሰምተነዋል ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር እና ህዝቧን ከመከራ፣ ከስቃይ፣ ከስደት፣ ከመበታተን፣ ለመታደግ እውነትን  መምረጫችን ሰዓት ላይ ነን። ትኩስ አልያም በራዱን መሆን ይጠበቅናል ነገር ግን ትኩሱም በራድም ሁለቱን መሆን ግን በአሁኑ ሰዓት አይሰራም። *ትኩሱም በራዱም ስላልሆንክ ልተፋህ ነው የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል መጥቀሱን አስፈላጊ ነው። ወይ እውነትን ወይ ውሸትን ወይ ኢትዮጵያዊ አልያም ወያኔአዊ መሆን ግድ ይለናል ሁለቱ መሆን ከመጥፋት አያድንም።
ግዜው የስራ ነው። ለክርክር እና ውሸትን ለማስተናገድ ቁጭ ብለን የምናስተናግድበት ግዜ አልፋል። ጉንጭ አልፋን የወያኔ ዲሞክራሲ ነኝ ክርክርም ሰዓቱ ተጠናቃል። መሰረቱ ውሸት የሆነ ድርጅት መሰረቱ የሚናድበት ሰዓት ላይ ነን ስርዓቱ ከስሩ የሚነቀልበት ግዜ ላይ ነን ለደቂቃም የወያኔን የውሸት ፕሮፖጋንዳ ለመስማት ግዜያችንን የምናጠፋበት ሰዓት አይደለም አሁን ወሬና ወሬ ብቻ የሆነ ነገሮችን ለመስማት ፍቃደኝነት አይኖረንም። ስለዚህ በረሃ የሚወርድ በረሃ ይወርዳል። ከተማ የሚቀርም ከተማ ይቅር። በገጠርም የሚቀመት ገጠር ይቀመጥ። ብቻ ቤትም በኩል በሁሉም አቅጣጫ ኢትዮጵያን ሲዘርፍና ህዝቦቻ ሲገድል ሲያስጨንቁ የከረመን የማፍያ ቡድን ለፍርድ የምናቀርብበት ሰዓት ላይ ነንና ሁሉም በአድነት ለአንዲት ኢትዮጵያ የምንቆምበት ግዜ ነው።
ወያኔ ፕሮፌሰር ብርሃኑን የተለየ የውሸት ስም ቢለጥፍበትም የወያኔ ተንኮልና ውሸት ከኢትዮጵያን አልፎ የአለም ህብረተሰብ የተረዱበት  ስለሆነ በከሰረ ፖለቲካ ውስጥ በመደናበር በአልሞት ባይ ተጋዳይ እየተፍጨረጨረ ነው። የነጻ ሚዲያዎችን እንደ ኢሳት ቪኦኤ የጀርመን ራዲዮ የመሳሰሉን ለማፈን በቢሊዮን የሚቆጠር የአገሪቷን ንብረት ቢያባክንም ሊሳካለት አልቻለውም። አርበኞች ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ነው ብሎ ለምዕራቢያኑ ቢከስም የትኛውም አገር ሊቀበሉት አልቻሉትም የፖለቲካ ኪሳራ ማለት ይህ ነው። የፖለቲካ ኪሳራ ማለት በአገር ቤት ህዝብ ሲቃወመው በውጭ አገር ሃያላን አገራቶች አጋርነታቸውን ሲነፍጉት የመውደቂያ ዋዜማ ላይ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ላይ በታላቅ ክብር የአውሮፓ ኃያላን መንግስታት ፊት በዋና ተናጋሪነት መጋበዝ የወያኔዎችን የወገብ ጅማቶቻቸው በድንጋጤ የተፈቱበት ዜና ነው። ኢትዮጵያዊያኑ በክብር የሚያዩት ብርቅዪ የኢትዮጵያ ልጅ ሃብታም ነን ያለን ይበቃኛል ሳይል፡ የተማርኩኝ ነኝ ትምህርቴ ያኖረኛል ሳይል፡ ለኢትዮጵያ ክብር ሲል ለህዝብ ፍቅር ሲል ያለውን ክብር ሃብትና ዝና ትቶ ወደ በረሃ የወረደ በኢትዮጵያ ልብ ውስጥ የገባ በደም ስር ውስጥ የሰረጸ በኢትዮጵያ ፍቅር የተቃጠለ ኩሩ፣ ቆራጥ፣ ጀግና፣ የኢትዮጵያ  ነው። ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ወድ ህይወታቸው ከሰጡ ቆራጥ ልጆች መሃከል አንዱ የሆነው ብርሃኑ ነጋ ነው።
ብርሃኑ በአውሮፓ ፓርላማ ሊናገር የሚችለው ስናውቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልቡ በደስታ እና በብርሃን ተሞልታል /ወያኔዎች ግን በጭንቅ ውስጥ ናቸው። አሁን ወያኔን ይጭነቀው። በሰራው ግፍና በደል መልሱን የሚያገኝበት ግዜ በመምጣቱ አስደንግጦታል። እንቅልፍ የማይተኙበት ግዜላይም ነው። በዘረፉት የኢትዮጵያ ሃብት ሰቀቀን ውስጥ የገቡበት ነው። ደግመን ደግመን ያልነው ቀን ደረሰ። ደግመን ደግመን ያሳሳብነው እለት መጣ። ተው ተው የተሾመ ሁሉ ይሻራል ያኔ መውደቂያቹን እወቁ ያልንበት ሰዓት መጣ። የወያኔ ጉድ በአደባባይ ያውም በአውሮፓ ህብረት ፊት ለፊት ሊዘራ ነው። አውሮፓዊያኑ የአርበኞች ግንቦት 7 አላማ በግልጽ ሊረዱት ነው። ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብን እያሸበረ  እንደሆነ ሊነገራቸው ነው። የወያኔ በስልጣን መቆየት ለምስራቅ አፍሪካ መተራመስ ዋንኛ ጠላት እንደሆነ ምዕራቢያዊያን ሊረዱት ነው። አሁን ወያኔ የሚጫወታቸው የማስመሰያ ጌሞች አይኖሩትም ሁሉ ነገር ታውቆበታል።  ዶክተር ብርሃኑ ከአውሮፓ ፓርላማ ንግግር በኋላ የትግሉ ፍጻሜን የሚያሰማበት ቀን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠብቀው ነው። ሁሉም ለሚደረገው ጥሪ መዘጋጀት ብታ ነው የሚጠበቅበት በገዛ አገራችን ባርነትን ለማጥፋት የመጨረሻው ሰዓት በመድረሱ ወያኔን ለፍርድ ለማቅረብ ሁሉም መዘጋጀት አለበት።  ለኢትዮጵያ ራእይ ያለው ፕሮፌሰር ነጋ የሁል ግዜ የኢትዮጵያ ጀግና ነው።
መርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)
29.11.2015


No comments:

Post a Comment