Sunday, December 20, 2015

የአቡነ እንጦስ በኖርዌይ ቆይታ ሃይማኖታዊ ወይንስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ?

በለንደን በማበጣበጥ የተባረሩት አቡነ እንጦስ ኖርዌይ ምእመንን ለመከፋፈል ገብተዋል ፤አስቸካይ እርምጃ የሚጠይቅ ጉዳይ ነውና አንብበው በንቃት ተሳተፉ!!! ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ10፣ቁጥር 1 ላይ ''እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው'' ዮሐ ምዕ 10፣1 ብሎ አስተምሮናል።ይህ ቃል የሚያስተምረን ትልቅ ቁም ነገር አለ።በሃይማኖታዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ የሚመስሉ ነገር ግን ተግባራቸው የቆሙለትን የዘር ዘውግ ወይንም የንዋይ ጥማት ለማርካት ብቻ የሚፈልጉ አባት ያልሆኑ ነገር ግን በአባትነት ስም ቤተ ክርስቲያንን የሚያምሱ እንደሚነሱ ሲነግረን እነኝህ ሌባ ወንበዴ እንደሚባሉ እራሱ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]Abune Entose in Norway
http://ecadforum.com/Amharic/archives/15986/የአቡነ እንጦስ በኖርዌይ ቆይታ ሃይማኖታዊ ወይንስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ? '' በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው'' ዮሐ ምዕ 10፣1 በለንደን በማበጣበጥ የተባረሩት አቡነ እንጦስ ኖርዌይ ምእመንን ለመከፋፈል ገብተዋል ፤አስቸካይ እርምጃ የሚጠይቅ ጉዳይ ነውና አንብበው በንቃት ተሳተፉ!!! ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ10፣ቁጥር 1 ላይ ''እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው'' ዮሐ ምዕ 10፣1 ብሎ አስተምሮናል።ይህ ቃል የሚያስተምረን ትልቅ ቁም ነገር አለ።በሃይማኖታዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ የሚመስሉ ነገር ግን ተግባራቸው የቆሙለትን የዘር ዘውግ ወይንም የንዋይ ጥማት ለማርካት ብቻ የሚፈልጉ አባት ያልሆኑ ነገር ግን በአባትነት ስም ቤተ ክርስቲያንን የሚያምሱ እንደሚነሱ ሲነግረን እነኝህ ሌባ ወንበዴ እንደሚባሉ እራሱ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል። አቡነ እንጦስ አገር ቤት በሚገኘው በወያኔ በሚታዘዘው ሲኖዶስ ስር ሆነው በእንግሊዝ የሚኖሩ ምእመናንን በከፍተኛ ደረጃ ሲያበጣብጡ ከርመው ወደ ኖርዌይ በበሩ ሳይሆን በሌላ መንገድ ማለትም ምእመናን ሳያውቁ እና ጥቂት የጥቅም እና የጎጥ ዘውግ ተጋሪዎች እንዲሰሙ ተደርጎ ገብተዋል።ኖርዌይ ከገቡም ቀናት አስቆጥረዋል።ለመሆኑ አንድ በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ያለ አባት ከምእመናን ተደብቆ መግባት እና እራስን መሽሸግ ለምን አስፈለገ? በበር ለመግባት እና እንደ ሌባ ወይንም ወንበዴ እራስን መሰወር ለምን አስፈለገ? አቡነ እንጦስ በአገር ቤት ባሉ አባቶችም ጭምር በደህንነት ሰራተኛነት እንጂ በክህነት ስራቸው አይታወቁም አቡነ እንጦስ የታላቁን አባት የግብፁን ፃድቅ አባ እንጦስ ስም ይያዙ እንጂ ተግባራቸው ሌላ ነው። የአቡነ እንጦስን የወያኔ የዘር ፖለቲካ በቤተክርስቲያን አስገብተዉ ምእመናንን ሲያበጣብጡና ሲከፋፍሉ እንዲሁም በወ ያኔ የስለላ መረብ ከተሰማሩ ሰዎች መካከል አንዱ ሆነዉ በመገኘታቸው በእንግሊዝ የደህንነት መስሪያ ቤት በመረጋገጡ ከመንበረ ጵጵስና ድ/ቤታቸው ከለንደን በደህንነት ፖሊስ ተይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ ባለፈውዓመትማለትም በ2007ዓ .ም እንዲመለሱመደረጋቸውይታወሳል። የፈጸሙት ተግባር ከባድ በመሆኑ በሊቀ ጵጵስነታቸው የተሰጣቸዉን የዲፕሎማቲክ ያለመፈተሽ መብታቸው ተነጥቆ ዳግም ወደ እንግሊዝ አገር እንዳይገቡ የሚከለክል ምልክት ፓስፖርታቸዉ ላይ ተመቶ ባቸዋል። ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኃላም የአንድ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በአዲስ አበባ ወይም በክፍለ ሀገር ተመ ድበው እንዲሰሩ አልተደረገም። የወያኔ ስርአት በስልጣን እንዲቆይ የሚያስችለዉን የፖለቲካ ስራ በአገር ውስጥ እና በው ጭአገር ያሉ አብያተክርስትያናትን በካህን ካድሪነት መቆጣጠር ነው። በዚህም መሰረት አቡነ እንጦስ በስርአቱ ዉስጥ ባላቸዉ የፖለቲካ ስልጣን ከቤተክርስቲን መዋቅር ዉጪ 1ኛ፣ በአገር ውስጥ ለስርአቱ ታማኝ የሆኑ ትግሬ ካህናትንና ሌሎች ለጥቅም የተደለሉ አባቶችን በቤተክርስትያን አስተዳደ ር መዋቅር ውስጥ የምደባና ድልደላ ተግባራት እንዲከናውኑ 2ኛ፣ በውጭ አገር የውጭ አብያተክርስቲያናት የፖለቲካ ግንኙነት ክፍል ተጠሪ በመሆን በዉጭ አገር ከሌሎች የእምነት ተቃማት ጋር በስራ ጉብኝት ስም የሀይማኖት ካባ ለብሰው ስለወያኔ ስርአት መልካም አስተዳደርና ልማታዊ መንግስት የሚለውንዲስኩር ማስተዋወቅ አንዱ ሲሆን ሌላዉ ዋናው ስራቸው በአውሮፓ የሚገኙ ገለልተኛና. በስደተኛው ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ ቤተክርስቲያናትን ከተቻለ ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ወያኔ በሚቆጣጠረዉ አገር ዉስጥ ካለው ሲኖዶ ስ ስር ማስገባት ካልተቻለ ብጥብጥ በማስነሳት ከፊልምእመናንም ይዞ በአገር ቢቱ ሲኖዶስ የሚተዳደር አዲስ ቤተክርስ ትያን መመስረት ዋነኛዉ በዉጭ አገር ለአቡነእንጦስ የተሰጣቸው የፖለቲካ ተልእኮ ነው። የአቡነ እንጦስ በሌላ በር የገቡባቸው ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች ምክንያት አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በህውሃት አጉራ ዘለል ባለስልጣናት የግል ትዕዛዝ ንብረቷ እና ጥሬ ገንዘቧ ሲዘረፍ መኖሩ የአደባባይ ምስጢር ነው።አቦይ ስብሐት እና በአባይ ፀሐዬ የሚመራው የዘራፊ ቡድን በቤተ ክህነት ውስጥ መሽጎ የቤተ ክርስያንን ንብረት እየዘረፈ ይገኛል።ይህ ቡድን በቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ምእመናን ዘንድ ''የጨለማው ቡድን'' በመባል ይታወቃል።የጨለማው ቡድን በጎጥ ዘውግ እና በጥቅም ዙርያ የኮለኮላቸውን የቡድኑን አባላት ከቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት እስከ የጥቅም ተጋሪ ዲያቆናት እና የሰበካ ጉባኤ አሰማርቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ካለ ምንም ርህራሄ እየመዘበረ ይገኛል።የጨለማው ቡድን አባላት ውስጥ አቡነ እንጦስ አንዱ ናቸው።የጨለማው ቡድን አባል ለመሆን የሚፈለገው የአቦይ ስብሐት እና አባይ ፀሐዬ መንደር መወለድ እና/ወይንም ቤተ ክርስቲያንን ለመዝረፍ መዘጋጀት ይጠይቃል። የአቡነ እንጦስ አንዱ ወደ ኖርዌይ የመጡበት ጉዳይም ይሄው ነው።በስልጣን ሽኩቻ በሁለት የተከፈለው የበረከት ስምኦን ቡድንና የአርከበ ቁባይ ቡድን ችግር በቡድኑ ተከታዮች በሆኑ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አባቶች መካከል ሁለት ቦታ እንዲከፈሉ አድርጋቸዋል። በቤተክርስትያን አባቶች መካከል በተፈጠረው ክፍፍል በቤተክርስትያኗ ንብረት ላይ የዝርፊያው ውድድር እንደ ህወሃት ባለስልጣናቱ በተመሳሳይ በተፈጠረዉ አባቶች ቡድን መካከል ተጧጡፏል። በኢትዮጵያ የተፈጠረው የወቅቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ያሰጋቸው በዝርፊያዉ የተሰማሩ አባቶች ዘርፈው ያከማቹትን የቤተክርስቲያን ገንዘብ ወደ ውጭ አገር በማሸሽ ላይ ይገኛሉ።ከነዚህ አባቶች መካከል አቡነ እንጦስ አንዱ ናቸው። በንብረት ማሸሽ ስራ የተሰማሩት አቡነ እንጦስ የዘረፉትን የቤተክርስቲያን ገንዘብ ኖርዋይ ይዘው እንደገቡ ይታመናል። ሊሎች አባቶችም በተመሳሳይ የገንዘብ ማሸሹን ስራ ውጭ አገር ወያኔ በሚያስተዳድረው ሲኖዶስ ስር ያሉ ቤተክርስትያናትን ማአከል በማድረግ የማሸሹ ስራ ቀጥሏል። የእነዚህ ዘራፊ አባቶች ውጭ አገር አመጣጥ ሚስጢር ነው።ከስርአቱ ጥቂት ታማኝ ሰዎች ዉጭ መቼ እንደሚመጡ ለምእመኑ አይነገርም።ውጭ አገር ሲገቡ ግልጽ የሕዝብ አቀባበል አይደረግም። ከመነሻቸው እስክ መድረሻቸው ልክ እንደ ወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት በድብቅና በሚስጢር የተያዘ ነው።የአቡነ እንጦስ ኖርዋይ አመጣጥም የሆነው ይኸው ነው። ለምን በሚስጥር ማድረግ አስፈለገ? አንድ መንፈሳዊ የቤተክርስትያን አባት ለዚያውም ሊቀ ጳጳስ መቼ ቀን እንደሚመጡ ምእመን አዉቆ ቡራኪዎ ይድረሰኝ ብሎ አየር ማረፊያ ሂዶ አቀባበል ቢያደርግ መባረክ አያስፈልግ ይሆን? እውነት አመጣጣቸው ለቤተክርስትያንና ለኖርዋይ ምእመን መንፈሳዊ ህይወት ተጨንቀው ነውን? አይደለም።የመጀመርያው ምክንያት ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተዘረፈውን የውጭ ምንዛሬ ከአገር ይዘው ወጥተው ኖርዌይ መሽገዋል።ጉዛቸው የአቡነ እንጦስ ቡድን አባቶች እንጂ በሲኖዶሱ ፍቃድ እንዳልሆነ ይታወቃል። የአቡኑ እንቅስቃሲዎች አብዛኞቹ በስርአቱ ባለስልጣናት የሚወሰን ነው። ምክንያት ሁለት ሁለተኛው የአቡነ እንጦስ የኖርዌይ የጉዞ አላማ ደግሞ በጎንደርና ኦሮሚያ የተነሳዉ የህዝብ አመጽ ከቀጠለ በስደተኝነት በኖርዋይ ለመኖር መደበቂያ ከወዲሁ ማመቻቸት ነው።ችግሮች እየተባባሱ ሲመጡ ከተቃዉሞ ለመዳን ከወዲሁ ደጋፊና ተከታዮችን በኖርዋይ የማብዛት ዝግጅት ታስቦ ነው ።በእዚህም በጥቅም የሚጋሯቸውን እና ዘመዶቻቸውን በማሸሽ በቤተ ክርስቲያን ስም የእራስን ኑሮ የማደላደል አላማ የያዘ ነው።ከ15 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ተርቦ እና የሚቀመስ አጥቶ፣በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተው እና የካህን እና የእጣን ያለህ እያሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ጵጵስና ተቀብለው ምእመናንን ማፅናናት ሲገባ ከምእመናን ጉሮሮ የተሰበሰበ ገንዘብ ይዞ ከአገር መውጣት ወንጀለኘነት ነው። ምክንያት ሶስት ሶስተኛው የኖርዋይ የአቡነ እንጦስ ጉዞ ምክንያት ደግሞ መቀመጫዉን ሲዊድን ካደረገዉ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋር በመተባበር በኖርዋይ ያለውን በአገሩ ጉዳይ ግንበር ቀደም የሆነውን እውነተኛ ዜጋ እና ጽኑ ተቃዋሚ ሐይል ለማድከምና የስርአቱን አባልና ደጋፊ ለማብዛት እንዲቻል በኖርዋይ የሚገኙ ገለልተኛ ቤተክርስትያናትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የፖለቲካ ስራ ለመስራት ነው።በተለይ በቤተክርስቲያን ዙሪያ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ፍጹም ለቤተክርስትያን ስርአትና ለክርስትያኑ መንፈሳዊ ህይወት ተቆርቃሪና አሳቢ መስለው ምንም በማይነቃበት መልኩ የህይማኖት ካባ ለብሰው የፖለቲካ እንቅስቃሲውን ተፈጻሚ ለማድረግ ነው። ለዚህ የፖለቲካ ስራ የሚዉል የዉያኔ መንግስት የገንዘብ በጀት የመደበ ሲሆን ሰዎችን የገንዘብ ማባበያ ከመስጠት ጀምሮ አገር ቢት የተለየ ጥቅም የሚያገኙበትን ተስፋ የመስጠት አላማም ጭምር የያዘ ነው። በፊት ለፊት የማይመጣ እርሱ ሌባ ነው የአቡነ እንጦስ የአሁኑ ኖርዌይ አመጣጥ ከአሁን ቀደሙ ፍጹም የተለየ ነው።የአሁን ቀደሙ የሚመጡበት ቀን አስቀድሞ ተነግሮ ህዝብ አውቆት ኦስሎ አየር ማረፊያ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ነገር ግን ባለፈው ሳምንት የአቡኑ የኖርዋይ አመጣጣቸው በሚስጢር ነበር፤አስቀድሞ የሚመጡበት ቀን አልተነገረም፤ሲመጡም አቀባበልም አልተደረገላቸውም፤ ከመጡም በኃላ ከምእመን ጋር እንዲገናኙ አልተደረገም ፤ ከህዝብ ተደብቀው ለስርአቱ ታማኝ ከሆኑ ጥቂት ግለሰቦች ጋር ግንኙነታቸዉን ወስነው በድብቅ ይህን ጽሁፍ እስከምጽፍበት ሰአት ድረስ ለአንድ ሳምንት ያክል ተቀምጠዋል። ለምን አመጣጣቸውን በድብቅና በሚስጥር ሆነ! አዎ የሚስጢሩ ቁም ነገር በአሁኑ ጉዟቸው ብዙ የተዘረፈ የቤተክርስትያን ገንዘብ በማሸሽ ላይ እንደሆነ የታመናል፤ በሊቀ ጳጳስ ማእረጋቸው ዲፕሎማት ባለስልጣናት ሳይፈተሹ በሚያልፉበት ''ቪአይፒ'' በር ስለሚወጡ እያሸሹ ያለዉ ገንዘብ ያለ ምንም ችግር እንደሚያልፍ እርግጠኛ መሆን ይቻላል።በእርግጥ በድፍረት ያደረጉት ተሳክቷል። ሳይነቃ አልፎላቸዋል። ነገር ግን ኦስሎ አየር ማርፊያ የሚያሸሹት ገንዘብ ቢያዝባቸው ኖሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አባት በመሆናቸው ብቻ ቤተክርስቲያንና የእምነቱ ተከታዮቹ ሁላችን አንገት ያስደፋል ያሳፍራል።የጋዜጦች የመጀመርያ ገፅ አርስትም ልንሆን እንችል ነበር። የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንደሚባለው አቡነ እንጦስማ እንኳንስ ከኖርዌይ ከለንደን በእንግሊዝ የደህንነት ፖሊስ ተይዘው ኢትዮጵያ ተመልሰው የለ።ቤተክርስትያኗ ከመቸውም በላይ ፈተና ላይ ወድቃለች፤ቤተክርስትያኗንና ምእመኑን ሊመሩ በሚችሉ አባቶች በስሟ የሚነግዱ፤ ለፖለቲካና ለግል ጥቅማቸው የተመዘበረ ገንዘብ ማሸሺያ መሳሪያ ሆናለች። አርያነታቸዉን ባጡ አባቶች ምክንያት ኦርቶዶክሳዊያን አፍረዋል፤ተሸማቀዋል።የእምነቱ ተከታይ ላልሆኑ ሰዎች መሳቂያ ሆነዋል።ስለዚህ ሀይማኖታችን ለመጠበቅ ስርአተ ቤተክርስቲያን የሚጥሱና ቤተክርስትያንን ለግል ጠቅምና ለፖለቲካ ተልእኮ የሚያውሉ አባቶችን በግልጽ ልንነግራቸው ይገባል።የትህትናችንና የዝምታችን መጠን ቤተክርስትያንን፤አገርንና እምነትን እስከሚጎዳ ድረስ መሆን የለበትም።በተገቢው ሁኒታ በቃችሁ ልንላቸው ይገባል!!! የቤተ ክርስቲያንን ንብረት የዘረፈ የህሊና እረፍት የለውም።አቡነ እንጦስ አሁን ጭንቀት ላይ ናቸው ኖርዋይ ከገቡ በኃላ አቡነ እንጦስ ጭንቀት ላይ ናቸው።ያሸሸቱን ገንዘብ ለማስቀመጥ ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለመምረጥ ተቸግረዋል።ገንዘቡን ቦታ ለማስያዝ በኖርዋይና በሲዊዲን ታማኝ ሰዎችን፤የስርአቱ ቤተክርስቲናትና የንግድ ድርጅቶችን በማፈላለግ ስራ ተጠምደዋል።ባስተማማኝ ገንዘቡን ገና ባለማስቀመጣቸው ኖርዋይ ከመጡ ሳምንት ቢሆናቸውም ከህዝብ እስከሁን አልተቀላቀሉም። በአካል የሚገናኙት ከስርአቱ ታማኝ ጥቂት ሰዎችና ከአባ ቴወድሮስ ጋር ብቻ ነው።በአካል ከሚያገኛቸው ውስን ሰዋች በተጨማሪ ሌሎች ከሚያምኗቸውና ይቀርቡኛል ከሚሏቸው በኦስሎና በዙሪዋ ካሉ ጥቂት ግለሰቦች ጋር የስልክ ግንኙነት አድርገዋል። የአቡኑ መልእክት ኦስሎ ነዋሪ ለሆኑት- በአገር ቢቱ ሲኖዶስ ስር አዲስ በተቋቋመው ቤተክርስትያን ተሳተፉ የሚልና ከኦስሎ ውጭ ያሉ ገለልተኛ ቤተክርስትያናትን በአገር ቤቱ እንዲገቡ አባላትን አግባቡ እያሉ ሲሆን ከኦስሎ ውጪ ነዋሪ ለሆኑት ደግሞ በገለልተኛ ቤተክርስትያን የሚገለገሉ ታማኝ የወያኔ አባላትን፤ለትምህርት የመጡ ተማሪዎችን በስልክ ለስርአተ ቤተክርስቲያን የተቆረቆሩ በመምሰል በከተማችሁ ያለውን ገለልተኛ ቤተክርስቲያናት ወደ ወያኔ ሚቆጣጠረው ሲኖዶስ ማስገባት እንዳለባቸውና ሌሎችንም እንዲያስተባብሩ እየቀሰቀሱ ይገኛሉ። በቤተክርስትያን ላይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሽፋኑ ሐይማኖታዊ ይምሰል እንጂ ግልጽ የፖለቲካ ተልእኮ ያለው ነው። ምክንያቱም ከሚስጢራዊ አመጣጣቸው ጀምሮ ከህዝብ ተደብቀው ውስጥ ለውስጥ ከወያኔ አባላትና ደጋፊዎች የሚያደርጉት የአንድዮሽ ግንኙነት ሐይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ተልእኮ መሆኑ ማንም ይረደዋል።በተለይ ኖርዌይ ያለውን ጠንካራ ተቃዋሚ ሐይል ለማዳከምና የስርአቱን ደጋፊ ለማብዛት ቤተክርስትያንን ወያኔ በሚቆጣጠረው ሲኖዶስ በማድረግ ትግሉን ማዳከም ነው። በአገሩ ከስርአቱ ሸሽቶ በተሰደደበት ቦታ ዳግም ወያኒ በቤተክርስቲያን ስም ለመጨቆን መሞከሩ ድፍረት ነው። እውነት ለቤተክርስቲያንና ለምእመናን ነፍስ የተጨነቁ አባት ቢሆኑ ኖሮ በሰላም ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያንን የመንግስት ደጋፊና ተቀዋሚ በሚል በቤተክርስቲያን ለመከፋፈል ኖርዌይ ድረስ ከመምጣት ይልቅ እዚያው ኢትዮጵያ ከ15 ሚሊዮን በላይ በርሀብ ለሚያልቀው ህዝብ በጸለዩ ነበር፤ በጎንደርና ኦሮሚያ የሚፈጸመውን ግድያ የወያኔ ስርአት እንዲቆም ሽምግልና በጠየቁ ነበር። በተለይ በምድረ ኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን በተለይ በአካልም ሆነ በስልክ አቡነ እንጦስ ያነጋገራችሁ ግለሰቦች የአቡኑን ድብቅ አጀንዳና ተልእኮ በሚገባ ተረድታችሁ ሳንከፋፈል በአንድነትና በሕብረት ልንኖር ይገባል። የአቡነ እንጦስ ተልኮ ፖለቲካዊ እንጂ ሃይማኖታዊ አለመሆኑን ልትረዱት ይገባል። አቡነ እንጦስ በቤተክርስትያን ስም የወያኔን ካባ ለብሰው በኖርዋይ የሚኖሩ ኢትዮጵያንን የስርአቱ ደጋፊና ተቃዋሚ ብለው ለመከፋፈል በዋናነት ከሚጠቀሙባቸው ሰዎች መካከል አባ ቴዎድሮስ ይገኙበታል።አባ ቴዎድሮስ በኖርዌይ ያሉ ገለልተኛ ቤተክርስትያንን ወደ ገዢው ሥርአት ሲኖዶስ ለማስገባት ውስጥ ለውስጥ ከአባ እንጦስ ጋር መስራት የጀመሩት ከአንድ አመት በፊት ነው።ይሁን እንጂ አቡነ እንጦስ የማያውቁት አባ ቴወድሮስ በሚስጢር የያዙት ሌላ የግል ፍላጎት ነበራቸው።የአባ ቴወድሮስ ድብቅ ራእይ ለሰው አእምሮ ሊመች በሚችል መልኩ አንድነትና ሕብረት በኖርዋይ ያስፈልጋል በሚል ማታለያና ሽንገላ ኖርዋይ ያሉትን ቤተክርስትያን በሙሉ /በኦስሎ በስደተኛው ሲኖዶስ ስር ያለውን ቤተክርስቲያን ጨምሮ/ ገለልተኛ ቤተክርስቲያን ማድረግ ነበር። ሙሉ ኖርዋይን በገለልተኛ ቤተክርስቲያን በመቆጣጠር እንዲሁ በተመሳሳይ በውሮፓና አሚሪካ የገለልተኛ ቤተክርስቲያናትን በማስፋፋትና አቅምን በሲኖዶስ ደረጃ ከፍ በማድረግ የተደላደለ የግል ሕይወት መኖር ነበር።ሆኖም ይህ የሚሳካ አልሆነም።ስለዚህ ወደ ሁለተኛው ምርጫ ከአቡኑ ጋር ያለዉን ግንኙነት አጠናክረው ቀጠሉ። የአቡነ እንጦስ መንገድ ጠራጊዎች በአዲስ አበባ ያደረጉት ስብስባ አዲስ አበባ መስከረም ወር 2008 ዓ.ም አቡነ እንጦስ የሚመሩት የአባቶች ቡድን እና አባ ቴዎድሮስ ተገናኝተው በኖርዋይ ያሉትን ገለልተኛ ቤተክርስትያናት እንዴት ወቆጣጠር እንደሚቻል የመከሩ ሲሆን አባ ቴወድሮስ እነዚህን ቤተክርስያናት በገዢው ስርዓት ሲኖዶስ ስር ለማድረግ የሚያስችለውን ቅድመ ሁኒታ አመቻችተው እንደጨረሱ አቡነ እንጦስ ወደ ኖርዋይ መጠተው የቡራኪ ሥርአቱን እንደሚፈጽሙ የጋር ስምምነት ደርሰዋል። የስምምነቱን ተልእኮ ለማስፈጸም በአሚሪካ አገር አስተዳዳሪ ሆነው ለመስራት ከተስማሙበት ቤተክርስቲያን ጉዞ ሰርዘው አባ ቴዎድሮስ ወደ ኖርዋይ ተመልሰዋል።ለዚህ ወሮታ ዳጎስ ያለ ገንዘብ እና መኖሪያ እንዲሁም የክህነት እድገት እንዲሚያገኙ ለአባ ቲወድሮስ ቃል ተገብቶላቸዋል።ለዚህ የፖለቲካ ተልእኮ ታምነው ካስፈጸሙ የሊቀ ጳጳስ ማዕረግ እንዲሰጣቸው መፈለጋቸው ይሰማል።በአቡነ እንጦስ እና መሰሎቻቸው ዘመን ጵጵስና በብቃት እና በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑ ቀርቶል።ከቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ህይወት ይልቅ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙት አባ ቲወድሮስ አስቀድመው የተስማሙበትን ቤተ ክርስቲያን ከአሚሪካ መሂድ ቀረተው ኖርዌይ እንዲመለሱ ሲጠየቁ አላቅማሙም።የተሻላ ጥቅምና ስልጣን ያገኙበታልና።ለነገሩ አባ ቲወድሮስ አሚሪካ ሊሂዱበት ከነበረው ቤተክርስቲያን ምርቃት ወቅት የቅርብ ወዳጃቸው አባ ዘሚካኢል ከምእመኑ ተደብቀው ከግብዣው መገኘታቸው ችግርና ብጥብጥ ተፈጥሯል።በቤተ ክርስቲያን ሰላም መደፍረስ ጋር ተያይዞ ለቤተክርስትያናት ብጥብጥና ለምእመን መከፋፈል ምክንያት ከሆኑት አባቶች ውስጥ አባ ቴዎድሮስ ተጠቃሽ መሆናቸውን የሚገልጽ ዝርዝር ዘገባው በዚህ ሊንክ (http://ecadforum.com/Amharic/wpcontent/uploads/2015/11/zemecha-aba-melaku-3.pdf?bd378d) ይገኛል።በጽሑፉ ውስጥ አባ ቴዎድሮስ በስነ- ምግባር ብልሹ መሆናቸውን ቀደም ብለው በነበሩበት በአዲስ አበባ በምስካየዙናን መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን እና በኃላም በነበሩበት በተባበሩት አረብ ኤምሬት፣ በዱባይ በምእመን መካከል ግጭትና ብጥብጥ የፈጠሩ አባት ናቸው። በእዉነት አባ ቴወድሮስ ማን ናቸው? በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ የአንድ ገለልተኛ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸው።በኖርዌይ የሚገኙ ቤተክርስትያናትን በሙሉ ገለልተኛ በማድረግ በበላይነት ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ አባት ናቸው።ገለልተኛ በማድረግ አሳብ በግላቸው ታቦተ ጽላቶች ከኢትዮጵያ በማስመጣት በኖርዌይ ከተሞች ለሚገኙ ቤተክርስቲያናት በማከፋፈል የታወቁ ሰው ናቸው።ስርዓተ ቤተክርስቲያን በሚያዘው መሰረት በአገር ውስጥ ወይም በውጭ ሲኖዶስ ሊቀ ጳጳስ ታቦቱም ሆነ ህንጻ ቤተክርስቲያኑ እንዲባረክ አልተደረገም።ይህ ስርዓት ሳይፈጸም ቅዳሴውና ሌላው መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጣል። ለምን ብሎ የሚጠይቅ ምእመን የለም አባ ቲወድሮስ በጨዋታቸው የሚናገሩት አንድ ነገር አለ ይኸውም ከላይ በሲኖዶስ አባቶች ያልፈታ ችግር ስላለ ከዚህ ወይም ከዚያ ሳንል ገለልተኛ መሆን ይሻላል በሚል የዋህ ምዕመንን በማጭበርበር ነው። እውነት በምልኩስና ትምህርታቸው ይህን አይነት አስተምሮ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ትምህርታቸው ተምረውት ይሆን ! ገለልተኛ አቋም ቤተክርስትያናት እንዲኖራቸው ታቦታትን በኖርዋይ ከተማ ከማደል በተጨማሪ በውጭ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደረውን በኦስሎ የሚገኘውን ቤተክርስቲያን ወደ ገለልተኛ ቤተክርስቲያን ለመቅየር ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። በተለይ ኦስሎን መቆጣጠር ማለት ሙሉ ኖርዌይን መቆጣጠር ስለሆነ ያላቸውን ችሎታ ሁሉ ተጠቅመዋል።ይሁን እንጂ ሁሉንም የጥረት አማራጭ መንገዶች ቢጠቀሙም የኦስሎን ቤተክርስቲያን በቁጥጥራቸው ስር ማድረግ አልቻሉም።የአባ ቴወድሮስ መኖሪያ ኦስሎ ከተማ እስከሚመስል ድረስ ምእመናንን ለመከፋፈልና ለማጋጨት ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ አድርገዋል።የኦስሎ ቤተክርስቲያንን አቋም ወደ ገለልተኛ መቀየር ካልተቻለ ግን የኦስሎ ምእመን ዘጠና ዘጠኙ ፐርሰንት የንስሃ ልጆቼ ስለሆኑ ቤተክርቲያኗን እከፍላታለሁ የሚል ከአንድ አባት የማይጠበቅ የመከፋፈያ ፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ በከተማው ቢያስወሩም ምኞታቸው መክኖ ቀርቷል። ከቤተክርስትያን ዉጭ ቅስቀሳው ውጤት አላመጣ ሲላቸው በስታቫንገር ቤተክርስቲያን ላይ ደርበው ኦስሎ ላለው ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ልሁን ብለው ጠየቁ፤ይህም ሳይሆን ቀር ፤በመቀጠል በኦስሎው ቤተክርስቲያን ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ አባል ሆነው እንዲሰሩ ጠየቁ፤ይህም አልተሳካም።መድረክ አግኝተው ለመበጥበጥ የሚችሉበት ቀዳዳ መንገድ ሁሉ ተዘጋባቸው።መጨረሻም አባ ቲወድሮስ ኖርዌይ ያሉትን ቤተክርስቲያናት በገለልተኛ ስም መቆጣጠር እንደማይችሉ ተስፍ ቆረጡ። ይህ ከስርዓት ውጭ የቤተክርስትያንና የምእመናንን ሰላምና አንድነት የማፍረስ ተግባር በኖርዌይ በቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ፤በዱባይና በአትላንታ አሚሪካ በተመሳሳይ ፈጽመዋል።ከላይ በተጠቀሰው ሊንክ ጽሁፍ ውስጥ አባ ቴወድሮስ በአረብ አገር በዱባይ በነበሩት ወቅት የሥነ ምግባር ችግር የነበራቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ምስካዮ ሀዙናን ቢተክርስቲያን በነበራቸው ትንሽ ቆይታ የተምሮ ማስተማርን ማህበር ሲያማስኑ የነበሩና በአትላንታ ምእመናን በማጋጨት ስራቸው ሰይጣንን በእድሚ ቢያንሱ እንጂ በምግባር አይተናነሱም በማለት አባ ቲወድሮስን በአጭሩ አስቀምጣቸዋል። በኖርዋይ የገለልተኛ ቤተክርስቲያናት የበላይ አለቃ የመሆን ተስፋ የቆረጡ አባ ቴወድሮስ የስልጣን ጥማታቸውን ለሟሟላትና ኑሯቸውን ለማደላደል የወያኔ ስርዓት ከሚቆጣጠረው ሲኖዶስ ስር በቤተክርስቲያን የፖለቲካ ካባ ለብሰዉ የፖለቲካ ስራ ከሚሰሩ ካድሬ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንጦስ ጋር አብሮ መስራትን መረጡ።ባለፈው መስከረም ወር 2008 ዓ.ም አዲስ አበባ በተስማሙት ስምምነት መሰረት አባ ቴወድሮስ ኖርዌይ ከሚኖሩ የወያኔ አባላት፤ከኢትዮጵያ ለትምህርት ከመጡ ተማሪዎችና ሌሎች ከሥርዓቱ ደጋፊዋች ጋር በሚስጥር የአንድዮሽ ግንኙነት በማድረግ በኖርዌይ ያሉ ገለልተኛ ቤተክርስቲያናትን የወያኔ ባለስልጣናት በሚቆጣጠሩት ሲኖዶስ ለማስገባት በአካልና በስልክ የፖለቲካ ቅስቀሳቸውን ተያይዘውታል። አቡነ እንጦስ አስሎ ከመግባታቸው በፊትና በከገቡ በኃላም የቅርብ አማካሪ በመሆን የቅስቀሳዉን ስራ በዋናነት አባ ቴወድሮስ እየመሩት ይገኛል። በተለይ በአሁን ሰዓት አባ ቴወድሮስ በስታቫንገር የሚያስተዳድሩትን ቤተክርስትያን ጨምሮ በኖርዌይ ያሉ ገለልተኛ ቤተክርስቲያናትን በሙሉ ከአቡነ እንጦስ ጋር በመሆን ወያኔ በሚቆጣጠረው ሲኖዶስ ስር ለማስገባት በሚስጢር የወያኔ ታማኝ አባላትንና የሚያምናቸውን ሰዎች ስልክ እየደወሉ በቅስቀሳ ዘመቻ ስራ ተጠምደዋል። አቡነ እንጦስም በአባ ቴወድሮስ ጠቋሚነት በሚስጢር የአንድዮሽ የስልክ ቅስቀሳ በተመሳሳይ በማድረግ ላይ ናቸው። ተላላኪ ካድሬ ካህናት በትሮንድሂም ቤተክርስቲያን ገለልተኛ ቤተክርስቲያናትን ለመቆጣጠር አስመሳይ የወያኔ ካድሬ ካህናት በትሮንዲሂም ከተማ ቆይታ አድርገዋል። ሥርዓቱ በሚቆጣጠረው ሲኖዶስ ስር የማድረግ ዘመቻ እንቅስቃሴው የተደረገው አቡነ እንጦስ ኖርዌይ ከመግባታቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ነው።በአቡነ እንጦስና በአባ ቴወድሮስ አቀነባባሪነት በትሮንዳሂም የሚገኘዉን ቤተክርስቲያን ወደ ሥርዓቱ ሲኖዶስ ለማስገባት በተደረገው ድብቅ የፖለቲካ ዘመቻ ከጣሊያን አባ ዘድንግልና ከሲውዘርላንድ ዲያቆን ሰለሞን የሚባሉ የሥርዓቱ ሰዎችን በማስመጣት ነው።በዚህ የፖለቲካ ዘመቻ በትሮንዳይም የተሰማሩት አስመሳይ የወያኔ ካድሬ ካህናት ስምና ፎት። በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን በለንደን የተፈጠረዉ ብጥብጥና ከፍፍል በተመሳሳይ ኖርዌይ እንዳይፈጸም ጥንቃቄ ከወዲሁ እንድንወስድ ነቅተን ሁኒታዋችን እንከታተል።የወያኔ ባለስልጣናት በቀጥታ የሚቆጣጠሩት ቤተ ክርስቲያን ከወያኔ ፖለቲካ ተጽእኖ ነፃ አይደለምና ያሳደደን ሥርአት በሰላም በምንኖርበት አገር ዳግም በፖለቲካ እና በጥቅም በተዘፈቀ ሲኖዶስ ስም ሊከፋፍሉንና ሊለያዩን አይችሉም።በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች መሠረትበማድረግ የሚከተሉት አስቸኳይ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው። ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች 1. አቡነ እንጦስ ከለንደን ኢሚግሬሽን ፖሊስ ወደ ኢትዮጵያ ተገደው የተባረሩበት ምክንያት ከለንደን home office በሚገኝ ደብዳቤ መሰረተ ኖርዋይ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ባስቸካይ በተመሳሳይ ከኖርዌይ ለቀው እንዲወጡ ተጨማሪ ማስረጃ እንደተጠናቀቀ በአጭር ቀናት ውስጥ ክስ ለሚመለከተው አካል ይቀርባል፣ 2. ደብቀው ወደ ኖርዋይ ይዘው የገቡትን ገንዘብ በኖርዌይና ሲዊድን በሚኖሩ የአቡኑ ታማኝ ግለሰቦችና ንግድ ድርጅቶቻቸው እንዲሁም በስርአቱ ስር ባሉ የሲኖዶስ አብያተ ክርስቲያናት አከፋፍለው ሊያስቀምጡ በሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ስም የሚደረግ የገንዘብ ዝውውር ክትትል ማድርግና ማጋለጥ፤ማስረጃ ሲገኝ ክስ መመስረት፣ 3. የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣን አቶ ስብሃት ነጋ ''የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቢተክርስትያንን ጀርባ አከርካሪ አጥንት ሰብረናል'' ብሎ እንደመሰከረ ቤተ ክርስቲያን በግልጽ በገዥው ሥርአት በፖለቲካ ቁጥጥር ስር መሆኗን ራሱ ስብሃት የመሰከረና በግልጽ እንደምናየው የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ስር ያሉ አብያተ ክርስትያናት በወያኔ ባለስልጣናት አመራር የምትመራና የሀይማኖት አባቶች በስርአተ ቤተ ክርስቲያን ለመምራት በተጽእኖ ስር ናቸው።ይኸው የስርአቱ ሲኖዶስ በኖርዋይ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን ለመቆጣጠር መሞከር ማለት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የፖለቲካ ካባ ለብሶ በተሰደድንበት አገር ዳግም ነጻነታችንን ለመግፈፍ የሚደረግ የወያኔ ፖለቲካ ተጽእኖ ስለሆነ በህግ አግባብነት ያለውን እርምጃ በሚያስተባብሩ ሰዎች ለመውሰድ ሰዎቹን ማንነት ስምና አድራሻ መያዝ፣ 4. በአቡነ እንጦስ በድብቅ ወይንም በተናጥል በአካልና በስልክ ግንኙነት ያደረጋችሁ የአቡኑን የፖለቲካ ተልእኮ ያልተረዳችሁ የዋህ ጥቂት ሰዋች በመካከላችን ያለውን ሰላምና አንድነት እንዳይጠፋና እንዳንከፋፈል ጉዳዩን በአንክሮ ልታስተዉሉ ይገባል።በስርአቱ ሲኖዶስ ስር እንሁን በሚል በአቡነ እንጦስ ፖለቲካ ተልእኮ ማስፈጸሚያ ብትሆኑ ብዙ ስለ አቡኑ የማታውቁት ጉዳይ ከመኖሩ በላይ ከላይ ለተጠቀሱት ወንጀሎች ተባባሪ መሆናችሁን ልትረዱት ይገባል።ከሁሉም በላይ ደግሞ በኖርዌይ ያለነውን ምዕመናን ህብረት ለመለያየት እና በእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል የተወገዘውን የጎጥ ዘውግ ደጋፊ ወይንም የዘረኝነት አቀንቃኝ ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰረቀ ገንዘብ ተባባሪ መሆናችሁን ልትረዱት ይገባል።ከሁሉም በላይ ግን ሊቀ ጳጳሱ በአገር ቤት ባሉ አቻ ጳጳሳት ዘንድም ''የጨለማው ቡድን'' ተብሎ የሚታወቀው የቤተ ክህነቱ የወያኔ ተጠሪ አባላት ውስጥ የሚመደቡ መሆናቸው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። 5 በኢትዮጵያ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት የወያኔ ባለስልጣናትን እንዲሁም በቤተክርስትያን ንብረት ዘረፍ የተሰማሩ አባቶችን ያከማችቱን ገንዘብ ወደ ውጭ በተለያየ አገራት እያሸሹ ስለሚገኙ በየከተማችሁ የገንዘብ ዝውውርና ማስቀመጫ መንገዶችን በመከታተል አስፈላጊዉን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ነቅታችሁ ሌላዉንም እንድታነቁ ። በተልይ የወያኔ መንግስት በካድሬዋቹ በገለልተኛ ቤተክርስትያናት ላይ የከፈተውን የራስ የማድረግ ዘመቻ እንቅስቃሴ ግንዛቢ ወስደን ለሌሎች በማሰማት ቤተክርስትያናችን እንጠብቅ። ባጠቃላይ ከላይ በመነሻ አርዕስትነት ''እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው'' ዮሐ ምዕ 10፣1 እንደተጠቀሰው አቡነ እንጦስ ከህዝብ ተደብቀው መንቀሳቀሳቸው ‘’እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው’’ የሚለውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃልን በአካል ተመልክተንበታል።

No comments:

Post a Comment