ለአንድ ቀን ከአምስተርዳም ወጣ ብል፣ ምኑን ከምን እንደምጨብጠው ግራ ገባኝ- የኦሮምያ ወጣቶች ተቃውሞ፣ ጎንደር ማረሚያ ቤት፣ የሃይል መቆራረጥ፣ ረሃብ፣ ሃዋሳ ቤት ፈረሳ፣ጎርቻ ግጭት ፣ የሱዳን መሬት ከለላ ወዘተ። ደግሞ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ "በአውሮፓ ህብረት አልተጋበዙም" የሚል አስቂኝ ነገር አነበብኩ። እነዚህ ሰዎች ስለአውሮፓ ህብረት አሰራር እንኳን አያውቁም ማለት ነው? Hearing እንዴት እንደሚዘጋጅ ትንሽ ግንዛቤ የላቸውም? Hearing እኮ በእያንዳንዱ የፓርላማ አባል አነሳሽነት የሚዘጋጅ ነው። ታዲያ ግብዣው የወ/ሮ አና ጎሜዝ ብቻ ከሆነና ስብሰባውን ከናቁት ለምን አንድ የዋህ ወጣት ፈረንጅ የኢምባሲ ሰራተኛን " የመንግስታችንን አቋም አሳውቅልን" ብለው ወረቀት ጽፈው አስጨብጠው ላኩት? ያውም ተከላክሎ ላይከላከል። ( በዚህ አጋጣሚ መንግስት ፈረንጅ ወጣት ዲፕሎማት ቃል አቀባይ አድርጎ መወከሉ አገሪቱ የገባችበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳይ ነው።) ለማንኛውም ፕሮፌሰሩ ዛሬም የኮሚሽነሩን ሃላፊዎች አግኝተው አነጋግረዋል። እውነት ለመናገር በአውሮፓ ህብረት ትልቅ ስራ የሚሰራው ከመድረክ በስተጀርባ ባለ ኔትወርክ ነው። ሁሌም መርሳት የሌለብን ግን ትግሉ የራሳችን መሆኑን ነው። እኛ ነን እኛን ነጻ የምናወጣው።
No comments:
Post a Comment