Monday, December 7, 2015

ፋሲል የኔአለም

የኦሮሞ ህዝብ ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል አንድ አካል ነው። ነገ የኢትዮጵያ ታሪክ ሲጻፍ ይህም ትግል አብሮ ይወሳል። እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግሉን እንደግፍ። እጅ ለእጅ ካልተያያዝን ግን እጃንን እየነጠሉ በመቁረጥ እጅ አልባ ያደርጉናል። በኦሮሞ ህዝብ ትግል ፍርሃት ያለባችሁ ወገኖች፣ አብሮ ለዘመናት ተከባብሮና ተፋቆሮ እንዲሁም ተዋልዶ የኖረውን የኦሮሞን አርሶአደር አስቡ። የሊህቁን ( ኤሊቱን) ጸብ የመላው ህዝብ ጸብ አድርገን አናቅርበው። ያሳለፍነው ታሪክ ከሊህቁ የውዝግብ ታሪክ በላይ ነው። በረጅሙ ታሪካችን ብዙ ድሎችን በጋራ ጽፈናል፣ ብዙ መከራዎችንም በጋራ አሳልፈናል። የ አድዋን ታሪክ በአንድነት የጻፍን የአንድ እናት ልጆች ነን። ሊህቁ በጥራዝ ነጠቅ ትምህርቱ ታሪኩን እየደመሰሰ፣ የልዩነት ታሪክ ቢፈጥርም ህዝቡ ግን አሁንም፣ አፈሩዋን አፈሬ ብሎ ታሪኳንም ታሪኬ ብሎ አብሮ በአንድ ጎጆ ስር እየኖረ ነው። አሁንም እላለሁ- የሚገደሉት የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የእኛው ስጋ፣ አጥንትና ደም ናቸው። በጋራ እንጩህ!
ፋሲል የኔአለም

No comments:

Post a Comment