Saturday, December 12, 2015

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድምፅ ሬድዮ ጀግናው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት በወያኔ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ!!


የአርበኞች ግንቦት ሳበት ሰራዊት ተደጋጋሚ የሽምቅ ውጊያዎችን በማድረግ የህወሃትን መከላከያ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡
ባለፈው ሳምንት ህዳር 21/2008 ዓ.ም ጀግናው ሰራዊታችን በዋልድባ በጠላት ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዋልድባ ወደ አዲ-አርቃይ በመወርወር ማክሰኞ ህዳር 28/2008 ዓ.ም አዲ-አርቃይ ላይ ከወያኔ መከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል ጋር ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ እስከ 1፡00 ለሶስት ተከታታይ ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ በማድረግ በጠላት ላይ ሙትና ቁስለኛ በማስቆጠር ከፍተኛ ድልን ተጎናፅፏል፡፡
ሰራዊታችን በጦር ሜዳ ውሎው፣ከጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት በተቀዳ ወኔ፣እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የወያኔን መከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል በጦር ሜዳው ላይ በጥይት ቆልቶና አሳሮ አስቀርቶታል፡፡
ፍልሚየው በማግስቱ ረቡዕ ህዳር 29/2008 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ሰዓታት ማለትም እስከረፋዱ አራት ሰአት በዚያው አዲ-አርቃይ ላይ የቀጠለ ሲሆን ፣ ወያኔ ከሌላ ቦታ አጓጉዞ ለጦርነት ያሰለፈውን ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ጀግናው የአርበኞች ግንቦት ሰባት የነፃነት ታጋይ
የጠላትን ጦር ድባቅ በመምታት በመጣበት ሳይመለስ እንደ ወጣ አስቀርቶታል፡፡

ለነፃነት የሚደረገው ጦርነት አሁንም ቀጥሏል፡፡የወያኔ ባለስልጣናት የሚዙት የሚጨብጡት አጥተው በተለይ በኤርትራና በኢትዮጰያ መካከል የሚገኘውን ድንበር የበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሰራዊት ለመዝጋት ቢሯሯጡም ድንበር ላይ የተመደበው ወታደር ከወያኔ እየከዳ የነፃነት ትግሉ ከነትጥቁ በመቀላቀሉ ስልጣኑን ለሚዘውሩት ከፍተኛ ባለስልጣናት የራስ ምታት ሁኖባቸው ይገኛል፡፡
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት በተቀዳጀው ድል የአካባቢው ህዝብ ጮቤ እየረገጠ እደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ጀግናው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት ህዝቡን ከጎኑ በማሰፍ፣ በህዝብ ድጋፍ ታጅቦ ወደ መሃል አገር እየገሰገሰ ነው፡

No comments:

Post a Comment