Thursday, December 3, 2015

በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች ተቃውሞው ቀጥሏል -

አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች መቀጠሉ ተሰማ:በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች በሚገኙ ከፍተኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተቀጣጠለው ተቃውሞን ለመበተን ፖሊስ ሃይል ቢጠቀመምም የሕዝቡ ቁጣ አሁንም እንዳየለ ተገልጿል:: በበደኖ አደባባይ የወጣው ተቃውሞን ፖሊስ ለመበተን በወሰደው እርምጃ በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን የደረሰን መረጃ ሲያመለክት በተመሳሳይም በነጆ እና በነቀምቴም ፖሊስ ተማሪዎቹን ለመበተን በወሰደው እርምጃ መጎዳታቸውም ተሰምቷል:: በሆለታም እንዲሁም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተነሳው ተቃውሞ ወጣት ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል:: ተቃውሞው ከፍተኛ እንደነበር የሚገልጹት ዘገባዎችም በርካታ ተማሪዎች በፖሊስ ቆመጥ መቀጥቀጣቸውን አስታውቀዋል:: የተማሪዎቹ ጥያቄ ከማስተርፕላኑ በተጨማሪ ፌደራል ፖሊስ እየፈጸመ ያለውን ግድያ እንዲያቆም የሚጠይቅም ሆኗል:: በሌላ በኩል በደቡብ ኦሮሚያ ቡሌ ሆራ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ተቃውሞን ለማብረድ የተማሪዎች ተወካዮች እና የከተማው አስተዳደሮች ስብሰባ ቢቀመጡም ሊስማሙ አለመቻላቸው ታውቋል:: በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች አለመረጋጋቱ እንደቀጠለ ነው:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48689#sthash.uZTLcdQR.dpufHospital:

No comments:

Post a Comment