ችጋር የወለደው፡
ወሮበላው የወያኔ መንግስት ነኝ ባይ ፡በሀገራችን ላይ ካደረሰው ጉዳት ዋና ዋናዎቹ መግደል፤ ማሰር ህዝቦችን ለስደት የሚዳርጉ ና
ለራሳቸው ጥቅምና ሀብት ማፍሪያ አድርገው፡ ሊላውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ፡በመመልከትና የብቀላን ብትር በማሳረፍ
አስተዳድረዋለው በሚለው ህዝብ ላይ የሰቆቃ ብትር እያሳረፈበት ይገኛል። በነገራችን
ላይ የመሬት ቅርምቱ የገበሬውን የእርሻና የመኖሪያ ቦታዎች በመቀማትና ከንብረቱም ከኑሮውም ሳይሆን ሜዳ ላይ ከነቤተሰቦቹ በትኖ በማስቀረት ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በከተሞችም በተለይም በአዲስ አበባና አካባቢዋ እጅግ ብዙ የሚዘገንን የመሬት ዘረፋ እየተካሄደ ነው፡፡ የአምሳና ዐርባ ዓመት ይዞታ ያለውን ሰው አንድ ወያኔ በጨበጣ ይመጣና ያፈናቅለዋል፡፡ ይህ ወያኔ፣ ከሆነ ቦታ ማዘዣ ሊይዝ ይችላል ወይም በፌዴራል ሊያስገድድም ይችላል፡፡ “ሁሉ በጁ
ሁሉ በደጁ” በመሆኑ የፈለገውን
ለማድረግ፣ ቀልቡ ያረፈበትን መሬት ከዕድለቢስ ምሥኪን ኢትዮጵያዊ ወገኑ ለመቀማት ብዙም አይቸገርም፡፡ ለድሃ መጣሁ የሚለው ወያኔ በሰውነቱ ውስጥ በተካሄደበት ኬሚካላዊ ለውጥ በ24 ዓመታት ጊዜ
ውስጥ የለዬለት ፀረ-ድሃ ሆነና የማይፈጽመው ግፍና በደል የማናየውም የድሆች ብሶት የለም፡፡ ዱሮ በትግሉ ዘመን በዐይኔ ሂዱብኝ እንዳላለ፣ ዛሬ ወያኔ ስኳር ሲቀምስ ድሃ አልይ አለና ከጥቂቶች ጋር በሂልተንና ሼራተን አሼሼ ገዳሜውን ከአዳዲስ ባልንጀራዎቹ ከነአላሙዲንና አብነት ጋር ማጧጧፉን ቀጠለ፡፡ አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት የሚሊዮኖች ሲዖል የጥቂቶች ግን ገነት ሆና ሌላው ቀርቶ ከሰባትና ስምንት ዓመታት በፊት ደህና ነዋሪ የነበሩ ዜጎች ዛሬ በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ደረጃቸው ወርዶ የለዬላቸው ለማኞች ሆነዋል፡፡ የወያኔ መቶ ብር ምንዛሬ የደርግን አምስት ብርና የኃይለሥላሴን ሃምሳ ሣንቲም (ኧረ እንዲያውም
ከዚያም በጣም ያንሳል) በሆነበት ሁኔታ
የሦስትና አራት ሺህ የተጣራ ደሞዝ ተከፋዮች ይህ ገቢያቸው ከቤት ኪራይና ከጓያ ሽሮ እንዲሁም ከትራንስፖርት አላለፈም፤ እናም ይህ የወያኔዎች መሠረታዊው ድል በመሆኑ ሊኮሩበትና ሊኮፈሱበት ይገባል፡፡ ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከልቡ የሚወዳቸውና ጠብ እርግፍ የሚልላቸውም ለዚህ ድል ስላበቁት ነው፡፡ አዲስ አበቤ ስለሳቀና ‹እኝ› እያለ
ጥርሱን ስላገጠጠ ብቻ እየኖረ ያለ ሕዝብ ከመሰለን ስህተት ነው፤ ብዙዎቻችን እያኗኗርን እንጂ እየኖርን አይደለንም፤ አሸር በአሸር በልቶ እንደከብት መኖርን መኖር ካላችሁትም በዚህ ደረጃ የምንኖር በብዛት አለን፤ የለየላቸው ያጡ የነጡ ደግሞ በሥውር የርሀብ ጦርነት አንጀታቸው እርስ በርሱ እየተፋተገ የመሞቻቸውን ጊዜ የሚጠብቁ በየጎዳናውና በየቤቱ ሞልተዋል፡፡ አንዳንድ ጣዕረሞቶች ደግሞ በተፈጥሯቸው አስቸጋሪ ከመሆናቸው የተነሣ የሟቹን የመሞቻ ቅጽበት ለመተንበይ ያስቸግራሉ፡፡ ለዚህም ነው -ለምሳሌ- ለ24
ዓመታት ያጣጣረን አንድ ሰው በየትኛዋ ደቂቃ እስትንፋሱ ልትወጣ እንደምትችል መገመት የሚያቅተን፤ ነግር ግን ይህ ሰው አልሞተም ብሎ መዋሸት አይቻልም፡፡ ሞቱን ሞቷል፤ ችግሩ ዕድሩ አልለፈፈም፤ ለቀስተኛውም አላወቀለትም፡፡ አይደለም እንዴ ጓዶች?ይህን በደልና ግፍ በቃ ልንለው ይገባል የወገኖቻችንን በደልና ስቃይ የኔ
ነው፡ በማለት የተቀጣጠለውን ትግል ማንኛው ኢትዮጵያዊ በሀይማኖት፤ በቋንቋ ሳይለያይ በአንድነት ሆነን ለአንዴና ለመጨረሻ ወደ መቃብሩ
በማውረድ ለወገኖቻች እንድረስ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
No comments:
Post a Comment