Thursday, December 3, 2015

መንግስት በጎንደር የ17 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን አመነ * አንዱን የገደልኩት እኔ ነኝ ብሏል -

gonderየዜና እወጃ በጎንደር በ እስር ቤት ላይ በደረሰ ቃጠሎ የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ዘግበን ነበር:: መንግስት አንድ ሰው መግደሉን ሲያምን ሌሎቹ 16 ሰዎች ህይወት የጠፋው በቃጠሎው ወቅት ከ እስር ቤቱ ለማምለጥ ሲጋፉ ነው አለ:: የአማራ ክልል ፖሊስ ለመንግስት ሚድያዎች በሰጠው መግለጫው ትናንት ህዳር 21፣ 2008 በጎንደር ማረሚያ ቤት ከቀኑ 7፡30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ከማረሚያ ቤቱ ለመውጣት በተደረገው ግፊያ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ሊያመልጥ ሲል ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገልጿል:: እንደ አይን እማኞች ገለጻ ከሆነ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር ከ30 በላይ ቢሆንም መንግስት ቁጥሩን ማሳነሱንና በ እጁ የጠፉትን ቁጥር ወደ አንድ ብቻ ማሳነሱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል:: እንደ እማኞች ገለጻ አብዛኛው እስረኛ በመንግስት እጅ የተገደለ እንጂ ከ እስር ቤት ከ እሳት ለማምለጥና ለመውጣት ሲጋፉ አይደለም:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48682#sthash.Bs3LKWEn.dpuf

No comments:

Post a Comment