Monday, December 7, 2015

የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱት የሀይል እርምጃ ዓለም አቀፍ ውግዘት ገጠመው፣በአዲስ አበባ መሬት ዝርፊያ ስማቸው በቀዳሚነት የሚነሳው ወ/ሮ አዜብ መስፍን የማስተር ፕላኑን በመቃወም የተገደሉ ተማሪዎችን ጉዳይ አናናቁ ፣ዕቅዱን ጀምረነዋል እንጨርሰዋለን ሲሉ ዝተዋል፣ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች፣ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ፣አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ ፣ ቃለ መጠይቅ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እና ከፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ነጌሳ ኦዶ ጋር በወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና የተወሰደው የግፍ እርምጃ ላይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን

የተማሪዎቹ ጥያቄ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው።የመብት ጥያቄ ነው። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸው ሲቸገሩ ሲፈናቀሉ ከመሬታቸው ሲነሱና ሲቸገሩ ያዩ ናቸው።ብሶትነው ያስነሳቸው።በምንም መንገድ በዚህ አካባቢ ሌላው አይኑር አይደለም።የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው ጋር አብሮ በሰላም የኖረ ወደፊትም የሚኖር ነው።እነሱ በየጊዜውስንት ነገር ለማቀጣቀጠል ሕዝቡን ከሕዝብ ለማጋጨት ሞክረው አልተሳካላቸውም።ሕዝቡ አብሮ የኖረ ይሄን የተረዳ ሕዝብ ነውዓለም ገና ላይ በማይክራፎን የሌላብሄር ተወላጅ የሆናችሁ ስብሰባ ውጡ ብለው ኦሮሞ ሊያጠፋችሁ ነው የሚል ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር ይሄ የዚህ ስርዓት ውሸትና ፕሮፖጋንዳ ነው…>
አቶ በቀለ ነጋ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮዋና ጸሐፊ በኦሮሚያ ክልል የአገዛዙን ማስተር ፕላን ማሻሻያ በመቃወም ሰልፍ ወጥተው ስድስት ተማሪዎችየተገደሉበትን የተቃውሞ እንቅስቃሴና የአገዛዙን ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት ያሰበ ቅስቀሳ በተመለከተ ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን የግፍ ግድያ በመቃወም የተጠራው የሐሙሱ ሰላማዊ ሰልፍ በሚኒሶታ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ከተሞች ይደረጋል። የኦሮሞብሄር ተወላጅ ብቻ ሳይሆን ሰው ሁሉ የሆነ ሁሉም በአንድ ላይ እንዲቃወመው በተማሪዎቹ ላይ የተወሰደው የጭካኔ እርምጃ እንዲያወግዘው ያስፈልጋል  …ብሄርንከብሄር ለማጋጨት የሚሞክሩት የሚያወሩት ላይ ትኩረት ማድረግ አያስፈልግም በአንድ ላይ ተቃውሞን ማሰማት ያስፈልጋል…>
አቶ ነጌሳ ኦዶ የኦፌኮ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ በመጪው ሐሙስ በተለያዩ ከተሞች ስለተጠራው በኦሮሞ ተማሪዎች  ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወምሊካሄድ ስለታቀደው ሰላማዊ ሰልፍና ተያያዥ ጉዳዮች ከሰጡትን ቃለ መጠይቅ   የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ሁበር ሲያሽከረክዩ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ችላ ማለት ነጥብ ላይ የሚያመታው ተጽጨዕኖ አለ። ያንን መረዳት ያስፈልጋል። ነጥቡ ዝቅ ሲል ተመልሲመውጣት የሚችለው ሌላ የተሻለ ነጥብ መስጠት የሚችል ተሳፋሪ በሚሰጠው አስተያየት ወይም ነጥብ ነው። ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ግን አሉአሌክስአበራ በሳንፍራንሲስኮ በሁበር ብላክ ላይ የተሰማራ ሁበር በማሽከርከር ላይ የገጠሙትን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በተመለከተ ከሰተው አስተያየት(ሙሉውንአዳምጡ
<…በቬጋስ ሰላሳ ሁለት ዓመት ኖሬያለሁ። አንድ ቀን ቁማር ተጫውቼ አላውቅም። ያኔ ስመጣ ግርማ ጂሚ ስለ ቁማር የነገረኝ አይረሳኝም። ተመልከተው ይሄኛውንቁማር ይጫወታል ቤቱ ቴሌቬዥን የለውም ፣ይሄኛው ማደሪያ እንኳን የለውም ይሄኛው ቤቱ ቴሌቬዥን አለው አለኝ።ያኔ ቴሌቪዥን እንደ ትልቅ ነገር ነበር ለኛ። ከዛጊዜ ጀምሮ ቁማር እስካሁን አልተጫወትኩምበእኛ ጊዜ መንገድ የሚያሳየን ጠፍቶ ነው።ወጣቶች ታክሲ ላይ ሳያቸው እናለሁ።ስራው የትም አይሄድም ትምህርትቤት መሄድና መማር አለባቸው…>
አቶ ገዛኸኝ ተፈራ በቬጋስ የረጅም ጊዜ ነዋሪና 27 ዓመት ታክሲ ያሽከረከሩ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ ሁለተኛ ክፍል(ሙሉውን ያዳምጡት)
 በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት ሰሞኑን ሁለት ባልና ሚስት አሸባሪዎችበወሰዱት እርምጃ አንድ ሐበሻን ጨምሮ 14 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። እርምጃውን የወሰዱትአሸባሪዎች ማንነት እና አሳዛኙ ድርጊት ሂደትን በስፋት ዳሰነዋል (ልዩ ጥንቅር)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱት የሀይል እርምጃ ዓለም አቀፍ ውግዘት ገጠመው
በአዲስ አበባ መሬት ዝርፊያ ስማቸው በቀዳሚነት  የሚነሳው / አዜብ መስፍን የማስተር ፕላኑን በመቃወም የተገደሉ ተማሪዎችን ጉዳይ አናናቁ
ዕቅዱን ጀምረነዋል እንጨርሰዋለን ሲሉ ዝተዋል
ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች
ኢትዮኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ
አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑተገለጸ
 ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣  googel app store Hiber Radioወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

No comments:

Post a Comment