Saturday, December 26, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)



‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ በአገር ውስጥ በገጠመው እጅግ በጣም አስጊ ሁኔታ ምክንያት በሶማሊያ ተሰማርቶ የነበረውን የአየር ኃይል ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ውሳኔ ላይ ደርሶ ቡድኑ የጉዞ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታወቀ፡፡
====================================================
በሶማሊያ ከአሚሶም ጎን ለግዳጅ ተሰማርቶ የነበረው የህወሓት አየር ኃይል ቡድን እዚህ ግቡ የማይባሉ ሰባት አሮጌ ሄሊኮፕተሮች የነበረው ሲሆን ሶስቱ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ ተብሎ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ ሆኖም እስካሁን ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፤ የደቡብ ሱዳኑ ጉዞም መሰረዙ ተሰምቷል፡፡ ቀሪዎቹን አራት የሾቁ ሄሊኮፕተሮች የታጠቀው የአየር ኃይል ቡድን ደግሞ አሁን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ዝግጅቱን አጠናቆ የጉዞ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ 
የህወሓት አገዛዝ በኦሮምያ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ በጉልበት አፍኖ ለማርገብ በሱሉሉታ የተጠቀማቸው "የትራንስፖርት" ሄሊኮፕተር አብራሪዎች በጣም ዝቅ ብለው በመብረር ጭነዋቸው በነበሩት የአግአዚ ኮማንዶ አልሞ ተኳሾችና መትረየስ ታጣቂዎች ህዝቡን እንዲጨፈጨፍ አላደረጉም በሚል በግምገማ ተወጥረው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment