Wednesday, December 16, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
====================================================
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዛሬው ዕለት በጎንደር ወረዳዎች ከህዝቡ ጋር ሲያደርጉት የዋሉት ስብሰባ ያለምንም ውጤት ተበተነ፡፡
====================================================
በእነ አባይ ፀሐዬ እና በረከት ስምዖን እየተመራ ከአዲስ አበባ ጎንደር የገባው የአገዛዙ ከፍተኛ ሹሞች ልዑክ በጎንደር ከተማ፣ በመተማ ሸዲ፣ በጭልጋ እና በአርማጭሆ ከህዝብ ጋር ያደረገው ስብሰባ የባሰውኑ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል፡፡ በተለይም የመተማ ሸዲ ህዝብ "ቅማንትና አማራ ብላችሁ ከፋፍላችሁ እርስበርስ ልታጫርሱን ከመቀሌ የጦር መሳሪያ አስጭናችሁ አምጥታችሁ አከፋፍላችኋል..." በማለት በጥያቄ አፋጧቸዋል፡፡ 
በመጨረሻም ህዝቡ "እኛ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች ነን!" ሲል በአንድነት አቋሙን ገልፆ ከስብሰባው ፈርሶ ወጥቷል፡፡.

No comments:

Post a Comment