Saturday, December 5, 2015

ከሰበታ አከባቢ ለመለስ ዜናዊ መንደር ግንባታ 12 ሺህ ሄክታር መሬት መፍቀዱንና(የታዘዘውን መስማማቱን) የወረዳው አመራር የጻፈው ደብዳቤ ባለፈው ሳምንት ተጋልጧል።

ከሰበታ አከባቢ ለመለስ ዜናዊ መንደር ግንባታ 12 ሺህ ሄክታር መሬት መፍቀዱንና(የታዘዘውን መስማማቱን) የወረዳው አመራር የጻፈው ደብዳቤ ባለፈው ሳምንት ተጋልጧል። 12 ሺህ ሄክታር ማለት የሀዋሳን አንድ ሶስተኛ: የመቀሌን ግማሽ: የአዳማ(ናዝሬት) ሙሉ በሙሉ ስፋት ማለት ነው። ይህ መሬት ሲሰጥ የሚፈናቀለው አርሶ አደር: መድረሻ የሚያጣው ቤተሰብ ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። እኚህ ሰው(መለስ ዜናዊ) ሞተውም ማፈናቀሉን አልተዉትም። ለእሳቸው ክብርና ሌጋሲ ሲባል የስንቱ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ህይወት ግብር መጣል አለበት? የኢፍርት ኩባንያዎችን በአንድ ግቢ ለማሰባሰብ የታሰበ እንደሆነ ይገመታል።
ግፉ በዛ።
ተነጣጥሎ መታገሉ እስካልቆመ ገና የውርደት መዓት እንቀበላለን። ለሰበታው ገበሬ በደል የአርማጮህ ኢትዮጵያዊ ካላለቀሰ: ለሱዳን ለሚሰጠው መሬት የአምቦው ኢትዮጵያዊ ዘራፍ ካላለ: የኦሞ ሸለቆው መፈናቀልን የመቀሌው ወገን ካላወገዘ: የአፋር ዘላን ከቀዬው በልማት ሰበብ ሲባረር: አሶሳን ካላንገበገባት .......ነገ ሀገሪቱን ጨርሰው እኛኑ በቁማችን ይሸጡናል።


No comments:

Post a Comment