ትናንት ከጥቂት ወዳጆቼ ጋር ስለ ህወሃቶች አዲዎሎጂ ውይይት አድርገን ነበር። ብዙዎቻችን የተስማማንበት ጉዳይ የህወሃት ዋነኛ አዲዎሎጂ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ፋሺዝም መሆኑን ነው። የፋሺዝም ዋነኛ መገለጫ ባህሪ በብዙሃን ስም የጥቂቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ የበላይነት በብዙሃኑ ላይ በሃይል መጫን ነው። ፋሺዝም በሰው ልጆች እኩልነት፣ ነጻነት እና ፍትሃዊ ብልጽግና እና አስተዳደር ፈጽሞ አያምንም።
ከተቋቋመ ከ፵ አመታት በሁዋላም ህወሃት አሁንም የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ነኝ ብሎ እራሱን ያታልላል። ህወሃት በነጻነት ስም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፋሺስታዊ ቅኝ አገዛዝን ካሰፈነ ፪፭ አመታት ተቆጠሩ። የትግራይን ህዝብ ከማን ነጻ እንደሚያወጣ ቢጠየቅ እንኳ መልስ በአግባቡ ሊሰጥ አይችልም።
እውነታው ግን ህወሃት የኢትዮጵያን ህዝብ ገባር አድርጎ በዘር ሃረግ ከፋፍሎ ለጥዊቶች መጠቀሚያ የሆነች ኢትዮጵያ የምትባል የጥገት ላም እያለበ እንደመዥገር ደም እየመጠጠ ለመኖር ሲታገል ይህንን አጸያፊ ወንጀል ለማስፈጸም በኢትዮጵያዊያን ላይ እጅግ አስከፊ በደል እና ግፍ እየፈጸመ ከንቱ እድሜውን እየገፋ ይገኛል። ይሄ የማፍያ ድርጅትና መሪዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸውን ጥላቻ ዘውትር በሚፈጽሙት ግፍና በደል ከበቂው በላይ አስመስክረዋል።
አንድ የቅኝ አገዛ (internal colonialism) ሰለባ የሆነ ህዝብ ያለውን ነባራዊ እውነታ ተገንዝቦ ክብሩን፣ ነጻነቱን፣ ታሪኩን እና ማንነቱ ዘውትር እያረከሱ በጭካኔ እረግጠውና ቀጥቅጠው ሊገዙት የሚግተረተሩትን ወያኔዎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ሊዋጋቸው ያስፈልጋል። ስለዚህም ነው ወያኔን እና ቅጥረኛ የቅኝ አገዛዝ አስፈጻሚዎች ላይ ህዝባችን በህብረትና በአንድነት ከዳር እስከዳር ተነስቶ የጫኑበትን የቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል በቃ ብሎ መነሳት ያላበት።
እነሱ አሳሪ እኛ ታሳሪ፣ እነሱ ገዳይ እኛ ተገዳይ፣ እነሱ ዘራፊ እኛ ተዘራፊ፣ እነሱ ጌታ እኛ ሎሌ፣ እነሱ አባራሪ እኛ ተባራሪ፣ እነሱ ቅኝ ገዢ እኛ ቅኝ ተገዢ ሆነን መቀጠል ፈጽሞ አንችልም።
No comments:
Post a Comment